የቶዮታ መኪናዎች አምራች ከ2013 እስከ 2018 ባሉት አመታት ያመረታቸውን የራቭ4 መኪኖች ላይ የተገጠሙ ተቀያሪ ባትሪዎች አነስተኛ መጠን ያላቸው በመሆኑ መኪናዎቹ በፍጥነት በሚጠመዘዙበት ወቅት ቦታቸውን በመልቀቅ የባትሪው ፖዘቲቭ ከማያያዣው ጋር በመነካካት በሚፈጠር ብልጭታ መኪኖቹን ለእሳት አደጋ ሊያጋልጣቸው እንደሚችል ተጠቁሟል። በዚህ ችግር ተጠቂ ይሆናሉ የተባሉ ወደ 2ሚልየን ገደማ የሚጠጉ መኪኖች መፍትሄ እንደሚያስፈልጋቸውና መፍትሄው ሲዘጋጅላቸው በመኪና ሻጮች በኩል በነጻ ለደንበኖች እንደሚገጠም የቶዮታ አምራች ካምፓኒ ተናግሯል።
የመኪና አምራቹ አሁንም ድረስ ለዚህ ችግር መፍትሄ ለማበጀት እየሰራ እንደሆነና በዲሴምበር ለደንበኞቹ እንደሚያሳውቅ ተናግሯል።
ይህ ችግር የእናንተን መኪና ይመለከታል ወይስ አይመለከትም የሚለውን ለማወቅ በዚህ ሊንክ ሄደው ታርጋዎን ወይም የመኪናዎን ቪን በማስገባት ያረጋግጡ።