12/12/2024
Cheesebur Day (1)

ይህ ምርጫ በመላው አሜሪካ በጉጉት የሚጠበቅ ሆኗል። በአሁኑ ሰዓት የቨርጂንያ ሴኔት በዴሞክራቶች አነስተኛ የበላይነት የተያዘ ሲሆን ኮንግረሳቸው ደሞ በሪፐብሊካን አነስተኛ ብልጫ አለው። የነገው ምርጫ የአገሪቱን ጠቅላላ መራጮች አቋም መለኪያ ይሆናል ተብሏል።

ሪፐብሊካኖች በሁለቱ መወሰኛ ምክር ቤቶች ብልጫ ካገኙ የጽንስ ማጨናግፍን፤ የልጆች ስነ-ጾታና ተያያዥ ትምህርቶችንና የመሳሰሉትን በህግ እንዲቆሙ እንዲሁም የወላጆች በልጆቻቸው ስርዓተ-ትምህርትና በልጆቻቸው ጉዳይ የመወሰን መብቶችን ማስፋትና የስደተኛ መብቶችና ቅበላ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የመሳሰሉት ውሳኔዎች ያልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተቃራኒው ዴሞክራቶች ካሸነፉ በእነዚህና ሌሎች መሰል ጉዳዮች ላይ ያሉ ህጎችን ያላላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ቨርጂንያዎች ይበጀኛል የምትሉትን ነገ ወታችሁ ምረጡ። የመምረጫ ጣቢያችሁን ለማወቅ ሊንኩን ተከትለው አድራሻዎን ያስገቡ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት