ትላንት ጁን 15 ከሰዓት 5 ሰዓት በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ ኖርዝ ኢስት ፎርት ታተን አካባቢ በጋሎዌይ ስትሪትና ሳውዝ ዳኮታ ኖርዝ ኢስት አቅራቢያ ፖሊስ ኦፊሰሮች መኪና ውስጥ ስላለና ምንም ስለማይንቀሳቀስ ህጻን ተደውሎላቸው የደረሱ ሲሆን በደረሱ ሰዓትም ህጻኑ ህይወቱ እንዳለፈ አረጋግጠዋል።
የመኪናው አይነት ፎርድ ኤስ.ዩ.ቪ. እንደሆነ ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ እስካሁን የህጻኑን ሞት መንስዔ እያጣራ እንደሆነ፤ ለምን ያህል ሰዓት ህጻኑ መኪና ውስጥ እንደነበረ፤ ወላጆቹ የት እንደነበሩና የህልፈቱን መንስኤ እያጣራ እንደሆነ ታውቋል።
በወቅቱ የታዳጊው ሞግዚት አብረውት እንደነበሩም ታውቋል። አርብ የነበረው ሙቀት የህጻኑ ህልፈት መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ተጠርጥሯል።