12/12/2024
የሊሞ ሹፌር የሆነው ሚካኤል ጽጌ ድብደባና ዝርፊያ በዲሲ (13)

ዛሬ አርብ ጁን 14 ይኖራል ተብሎ በሚጠበቀው ከፍተኛ የሙቀት መጠን የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር የከተማውን ድንገተኛ የሙቀት አደጋ ፕላን ከእኩለቅን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን መመሪያ አስተላልፈዋል።
በዚህም መመሪያ መሰረት የአየር ሙቀቱ 95 ዲግሪ ወይንም ከ95 ዲግሪ ፋርኃናይት በላይ ከሆነ የከተማው መንግስት በየአካባቢው ጊዜያዊ የማቀዝቀዣ ማዕከላትን በማዘጋጀት ነዋሪዎችና ጎብኚዎች ራሳቸውን ለማቀዝቀዝ እንዲጠቀሙበት ክፍት ያደርጋል።


ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


የዚህን ዓመት የማቀዝቀዣ ጣቢያዎች ለማየት ይህን በመጫን ካርታውን መመልከት ይችላሉ።ከፍተኛ ሙቀት እጅግ አደገኛ ሲሆን እስከ ህልፈት የሚደርስ ጉዳት ያስከትላል። ራስዎን ከዚህ አደጋ ለመከላከል የሚከተሉትን ማድረግ ይመከራል።

በቂ ፈሳሽ ይጠጡ
ቢጠማዎትም ባይጠማዎትም ቀኑን ሙሉ ውሃ ይጠጡ።
ቡናና አልኮል መጠጦችን አያብዙ
መኪናዎን ከመቆለፍዎ በፊት በውስጡ ልጆችዎን፤ አዛውንት ቤተሰብዎን፤ አካል ጉዳተኛ ሰው ወይም እንስሳዎን አንዳልረሱ ያረጋግጡ። በፍፁም ሰው መኪና ውስጥ አስቀምጠው እንዳይወጡ።


ከፍተኛ ሙቀት በሚኖር ጊዜ ከቤት ውጪ ጉልበት ከሚፈልጉ ከባድ ስራዎችን ከመስራት ይታቀቡ። ግዴታ ከሆነ ደሞ አዘውትረው በጥላ ስር እረፍት ያድርጉ።
ቀለል ያሉ ልብሶችን ይልበሱ። የጸሀይ ጨረር መከላከያ ቅባት (ሰንስክሪን) ይጠቀሙ። ከቤት ውጪ ሆነው ሙቀቱ ካስቸገረዎ በመንገድዎ ላይ ያሉ የገበያ ቦታዎች(ሞል)፤ የህዝብ ላይብረሪዎችና የኮሚውኒቲ ማዕከሎች ውስጥ ይግቡና ራስዎን ያቀዝቅዙ።

ራስዎን ቤተሰብዎንና ጎረቤቶችዎን በሙቀት ተጎድተው እንዳይሆን ቼክ አርጉ። እንደ መፍዘዝ፤ ማዞር፤ ማቅለሽለሽ፤ ማስታወክ፤ መውደቅ (ፌንት-መንቀል)ና የጡንቻ መሸማቀቅ የሚመስሉ ስሜቶችን አስተውሉ። ነገሮች ከባሱ 911 ደውሉና እርዳታ ጥሩ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት