የቀድሞው ፕሬዘደንት ዶናልድ ትራምፕ የሜሪላንድ ሴኔት መቀመጫን ለመያዝ ከአንጀላ ኦልሶብሩክጋ እየተፎካከሩ የሚገኝትን የሪፐብሊካን ፓርቲው ላሪ ሆጋንን እንደሚደግፉ ዛሬ ለፎክስ ኒውስ አስታውቀዋል። ትራምፕ በዋሽንግተን ዲሲ ለፎክስ ኒውስ “[ላሪ ሆጋን] ሲያሸንፍ ማየት እፈልጋለሁ” ያሉ ሲሆን አክለውም “እንደሚመስለኝ ለማሸነፍ ጥሩ ዕድል አለው” ብለዋል።
ላሪ ሆጋን ከዚህ ቀደም የትራምፕ ቀንደኛ ተቃዋሚና ሀያስ እንደሆኑ ይታወቃል። ተንታኞችም ትራምፕ ላሪሆጋንን የደገፉት የዕውነት ድጋፋቸውን ለመስጠት ሳይሆን በለዘብተኞች ሊኖራቸውን የሚችለውን ድጋፍ ለማመናመን የታቀደ የክፋት ድጋፍ ነው ይላሉ።
የሜሪላንድን የሴኔት መቀመጫ የሚያሸንፈው ፓርቲ ዲሞክራቶችና ሪፐብሊካኖች በሴኔት አብላጫ ድምጽ ለሚያደርጉት ፉክክር ወሳኝ ነው።
ባለፉት 40 ዓመታት የሜሪላንድ የሴኔት መቀመጫ በዴሞክራቶች ብቻ ተይዞ የቆየ ሲሆን ላሪ ሆጋን ካሸነፉ ከ40 ዓመት በኋላ የመጀመሪያው ይሆናሉ።