Update: የውሀ አፍሉ ማስጠንቀቂያው ተነስቷል::
=============
በዋልተር ሪድ ድራይቭ ላይ ባጋጠመ የከፍተኛ ውኃ ተሸካሚ ቧንቧ መሰበር ምክንያት በአካባቢው ያሉ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ዛሬ አርብ ጁን 7 2024፣ በ2 ሰዓት ዘግይተው ይከፈታሉ ተብሎ የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ በወጣ. መግለጫ ትምህርት ቤቶቹ ዝግ ሆነው እንደሚውሉ ትነግሯል። ይህ መዘጋት የሚመለከታችው ትምህርት ቤቶች የሚከተሉት ናቸው። አቢንግደን፤ አሊስ ዌስት ፍሊት ኤለመንታሪ፤ አርሊንግተን ኬሪር ሴንተር፤ ባርክሮፍት፤ ክሌርሞንት፤ ሆፍማን ቦስተን፤ ሞንቴሶሪ ፐብሊክ ስኩል ኦፍ አርሊንግተን፤ ራንዶልፍ፤ ዌክፊልድና ትሬድስ ሴንተር ናቸው።
ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::
በተጨማሪም የቶማስ ጄፈርሰን፤ ሎንግ ብራንች ኤለመንታሪ፤ ኦክሪጅና ድሪው ኤለመንታሪ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በጊዜ ይለቀቃሉ።
በተጨማሪም በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች ውኃቸውን አፍልተው እንዲጠቀሙ ተመክሯል። የአርሊንግተን ካውንቲ ውኃ አፍልተው እንዲጠቀሙ የመከራቸው ሰፈሮች የሚከተሉት ናቸው። አልኮቫ ሀይት አንዳንድ አካባቢዎች፤ አርሊንግተን ሀይትስ፤ አርሊንግተን ሚል፤ አርሊንግተን ቪው፤ ባርክሮፍት፤ ክሌርሞንት፤ ኮሎምቢያ ፎረስት፤ ኮሎምቢያ ሀይትስ፤ ዳግላስ ፓርክ፤ ፎረስት ግሌን፤ ፎክስክሮፍት ሀይትስ፤ ግሪን ቫሊ፤ ፌይርሊንግተን፤ ፔንሮዝና ሺርሊንግተን ናቸው።
ይህ ማስጠንቀቂያ በእርግጠኛነት ውኃው መበከሉ ስለተረጋገጠ ሳይሆን ለጥንቃቄ እንደሆነም አክለው ገልጸዋል። በዚህም የተነሳ ይህ የውኃ ኃይል ማነስ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች የቧንቧ ውኃቸውን ሳያፈሉ እንዳይጠቀሙ አሳስቧል።
ካውንቲው ተገቢውን የላቦራቶሪ ምርመራ አድርጎ የውኃውን ጤነኛነት እስኪያረጋግጥ ድረስም ነዋሪዎች የቧንቧ ውኃ ሳያፈሉ እንዳይጠቀሙ መክሯል።
በነዚህ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?
- በቧንቧ ውኃ የተሰሩ በረዶዎችንና ሌሎች መጠጦችን ያስወግዱ
- ውኃ ከቧንቧ ሲወርድ ቀለሙን ከቀየረ ንጹህ ውኃ መፍሰስ እስኪጀምር ቧንቧውን ከፍተው ይተዉት
- የታወቁ የሊድ ምንጮች ካሉ ቀዝቃዛ ውኃ ለሁለት ደቂቃ ያፍሡ
- ውኃውን ቢያንስ ለ1 ደቂቃ በደንብ ያፍሉትና አቀዝቅዘው ይጠቀሙ
- የቀዘቀዘውን ውኃ በንጹህና በተሸፈነ ማስቀመጫ ያኑሩት
- በዚህ ወቅት ፈልቶ የቀዘቀዘ ውሃ ወይም የታሸገ ውሃ ብቻ ለሚከተሉት አገልግሎቶች ጥቅም ላይ መዋል አለበት፡
- ለመጠጥ
- ጥርስ ለመቦረሽ
- ምግብ ለማብሰል እና ማዘጋጀት
- ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ለማጠብ
- የሕፃናት ፎርሙላ ለማዘጋጀት
- በረዶ ለመሥራት
- ለቤት እንስሳት የመጠጥ ውሃ ለመስጠት
- በፍጹም የውኃ ማጣሪያ ማሽኖችን ብቻ ተማምነው ውኃ ከማፍላት እንዳይዘናጉ።
—-
ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶች ካሏችሁ ራሳቸውን ከበሽታ እንዲጠብቁ ይህን መረጃ አጋሯቸው።