በአሜሪካ ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ኖሯቸው 4ና ከዚያ በላይ አመት የኖሩ ነዋሪዎች ለዜግነት ማመልከቻ የኢንተርቪው መጠይቅ መልሶችን እንዲለማመዱ ታስቦ የተዘጋጀው ትምሀርት ምዝገባ ዛሬ ጁን 18 2024 ተጀምሯል።
- የሞንጎምሪ ካውንቲ ነዋሪ መሆን አለባቸው
- እድሜያቸው 18ና ከዚያ በላይ መሆን አለበት
- መሰረታዊ የእንግሊዝኛ ቋንቋን መረዳት አለባቸው።
- ሀጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ኖሯቸው 4 አመት በጋብቻ ከሆነ ደሞ 2 አመት ያለፋችው መሆን እንዳለባቸው ተነግሯል።
ትምህርቱ ጁላይ 9፣ 10፤ 11፤ 13ና 14 የሚጀምር ሲሆን ለ8 ሳምንት ይዘልቃል ተብሏል። ትምህርቱ ኦንላየን በዙም የሚከናወን ሲሆን አንዱ ክፍለ-ጊዜ በአካል በጌትስበርግ ላይብረሪ ሁለተኛ ፎቅ ይሰጣል። ይህ ዕድል ቀድመው ለተመዘገቡ እንዳመጣጣቸው ይሰጣል። ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ ወይም ከስር ያለውን ፎርም ይሙሉ።