ዛሬ ማክሰኞ ጁን 18 በመቶሺዎች ለሚቆጠሩና አሜሪካን ያለወረቀት እየኖሩ ላሉና በዋናነትም ከአሜሪካዊ ዜግነት ካለው ሰውጋ በጋብቻ ለተጣመሩ ሰዎች ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ እንዲያገኙ የሚያስችላቸውን ህግ አጽድቀዋል። ፕሬዘደንቱ ከሰሞኑ ባወጡት ሌላ ህግ በደቡባዊ ድንበር የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር በቀን ከ2500 ካለፈ ምንም አይነት የአሳይለም/ጥገኝነት ጥያቄ እንደማይቀበሉና ሁሉንም ስደተኞች ዲፖርት እንዲደረጉ የሚፈቅድ ህግ አጽድቀው የነበረ ሲሆን በዚህ ህግ ምክንያት በርካታ ነቀፋዎችን ከዴሞክራት ፓርቲ አባላት አስተናግደዋል።
2024 የምርጫ ወቅት እንደሞሆኑ አብዛኛዎቹ አዳዲስ ህጎች የመራጮችን ቀልብ ለመሳብ የታለሙ እንደሆኑ አንዳንድ ተንታኞች ይናገራሉ። የዛሬው ህግም የዚሁ አካል እንደሆነና፤ በተለይም የባለፈው ሳምንት ህግ ያስቆጣቸውን ደጋፊዎቻቸውን ቀልብ ለመሳብ ያሰበ ነው ይላሉ።
በዚህ አዲስ ህግ ተጠቃሚ ለመሆን አመልካቾች በአሜሪካን ከ10 አመት በላይ የኖሩና አሜሪካዊ ዜግነት ካለው ሰውጋ ከሰኞ ጁን 17 2024 በፊት ጋብቻ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል። ከዚህ በኋላ የሚያገቡትን አይመለከትም። ይህን ማመልከቻ አስገብተው የሚፈቀድላቸው አመልካቾች በ3 ዓመት ውስጥ ለህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ (ግሪን ካርድ)ና የስራ ፈቃድ ማመልከት ይኖርባቸዋል።