በኦውኒንግ ሚልስ ሜሪላንድ የሚገኘውና ቶታሊ ኩል የተባለ የአይስክሪም አምራች ምርቶቹ ሊስቴርያ ሞኖሳይቶጀንስ የተባለ በሽታ አማጭ ጀርሞች የመበከል እድል ሊኖራቸው እንደሚችል በማስገንዘብ ምርቶቹ ከገበያ እንዲወጡ አዟል፡፡ ምርቶቹን የገዙ ደንበኞቹም የገዙበት ቦታ እንዲመልሷቸውና ገንዘባቸውን እንዲመለስላቸው ወይም እንዲያስወግዷቸው አዟል፡፡
ሊስቴርያ ሞኖሳይቶጅን የተባለው ጀርም በታዳጊ ህጻናት፤ አዛውንቶችና የሰውነታቸው መከላከል አቅም የደከሙ ሰዎች ላይ እስከሞት የሚያደርስ በሽታ ያመጣል፡፡ ምንም እንኳ ጤነኛ ሰዎች ላይ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ህመም ቢያስከትልም ታማሚዎች ከባድ ትኩሳት፤ ከባድ የራስ ምታት፤ የሰውነት ጡንቻ መሸማቀቅ፤ ማቅለሽለሽ፤ የሆድ ቁርጠትና ተቅማጥ የመሳሰሉ ምልክቶችን ያሳያሉ፡፡
ምንም እንኳ ምርቶቹ በመላው አሜሪካ የተሰራጩ ቢሆንም እስካሁን በነዚህ ምርቶች አማካኝነት የመጣ በሽታ እንደሌለ የፌደራል መድሓኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ የምርቶቹ ባለቤት የሆነው ቶታሊ ኩል ኢንክ በዚህ ጀርም ተጠቅተዋል የተባሉ ምርቶቹን ማምረትም ሆነ ማከፋፈል ሙሉ ለሙሉ አቁሟል፡፡ በዚህ ጀርም ተበክለው ሊሆን ይችላል የተባሉ ምርቶችን ዝርዝርና ምስል ለማየት ይህን ይጫኑ፡፡
ጥያቄ ያላቸው ደንበኞች ደሞ በስልክ ቁጥር 410-363-7801 ወይም በኢሜይል regulatory@totallycoolicecream.com, ከሰኞ እስከ አርብ ከጧት 8 ሰዓት እስከ ከሰዓት 4 ሰዓት ባለው ሰዓት መደወል ይችላሉ ተብሏል፡፡