12/12/2024

Summer RISE በሞንጎምሪ የህዝብ ትምህርት ቤቶች (Montgomery County Public Schools (MCPS)) መሪነት በካውንቲው ከሚገኙ የንግድ ተቋማት፣ ከመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በዋናነት የካውንቲው የካፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ጁኒየር እና ሲኒየር ተማሪዎች በበጋው ወቅት በተጨባጭ ሙያ ላይ የተመሰረተ የስራ እድል ላይ እንዲሳተፉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል።

ተማሪዎች እንደምርጫቸውና ፍላጎታቸው በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ በመሳተፍ ስለተለያዩ የሙያ አይነቶች ተጨባጭ እውቀት እንዲያገኙ እድል ይኖራቸዋል።
የ Summer RISE 2022 ፕሮግራም ከጁላይ 5 እስከ ጁላይ 29 ድረስ ለ4 ሳምንታት የሚቆይ ሲሆን እያንዳንዱ ተሳታፊ ቢያንስ ለ50 ሰአታት በአካል፣ በርቀት (ቨርቿል) ወይም በሁለቱ ጥምረት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ ይሰማራሉ።

ተሳታፊ ተማሪዎች ከዚህ ፕሮግራም ምን ይማራሉ፡-

  • ድርጅታዊ መዋቅሮች እና አንድ ድርጅት በአጠቃላይ እንዴት እንደሚተዳደር
  • በተለመደው የስራ ቦታ አካባቢ የቀጣሪ ፍላጎቶች
  • የሙያ አማራጮች፣ የመነሻ ደሞዝ፣ ዲግሪዎች፣ የምስክር ወረቀቶች ወይም በአንድ የተወሰነ መስክ ውስጥ የሚያስፈልጉ ልምዶች
  • በንግዱ ማህበረሰብ የሚወሰኑ ሙያዊ እና ሊተላለፉ የሚችሉ የቴክኒክ ችሎታዎች
  • በማንኛውም ሥራ ላይ የሚተገበሩ ቴክኒካዊ እና ሙያዊ ከአንድ ስራ ወደ ሌላ የሚተላለፉ ክህሎቶችን ይማራሉ።

ለበለጠ መረጃና ለመመዝገብ ይህንን ይጫኑ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት