የNational Leased Housing Association (NLHA) የትምህርት ፈንድ የስኮላርሺፕ ፕሮግራም ማመልከቻዎችን መቀበል ጀምሯል። የNLHA የትምህርት ፈንድ የተቋቋመው በ2007 በናሽናል ሊዝድ ሃውዚንግ አሶሲዬሽን ሲሆን ዋና አላማው እንደ ሴክሽን-8 ባሉና በፌዴራል መንግስት ድጎማ በሚደረግባቸው የኪራይ ቤቶች ለሚኖሩ ነዋሪዎች የትምህርት ድጋፍ ለመስጠት ነው።
ይህ የስኮላርሺፕ ፕሮግራም ባለፈው አመት 48 ግለሰቦችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን ከተቋቋመበት ከ2007 ጅምሮ እስካሁን ድረስ ከ1 ሚሊየን ዶላር በላይ ፈሰስ በማድረግ ለአሸናፊዎች የትምህርት ክፍያ ወጪያቸውን ከፍሏል።
ይህ የስኮላርሺፕ ፕሮግራም እንደ ሴክሽን-8 ባሉና በፌዴራል መንግስት ድጎማ በሚደረግባቸው የኪራይ ቤቶች ለሚኖሩ ነዋሪዎች በ4 የተለያዩ ዘርፎች የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን የፕሮግራሙ አሸናፊዎችም ክፍያው በቀጥታ ለሚማሩበት ተቋም ይከፈልላቸዋል።
አመልካቾች ከሚከተሉት ምድቦች በአንዱ ስር ብቻ ማመልከት ይችላሉ፡
- The AIR Gives Opportunity Scholarship – ይህ ፕሮግራም በዋናነት የኮሌጅ ፍሬሽማን ወይም አቋርጠው የተመለሱ የአንደርግራጁዌት ተማሪዎችን ለማገዝ የታቀደ ፕሮግራም ነው።
- The Bill Gandert Memorial Scholarship – ይህ ፕሮግራም በዋናነት ለመጨረሻ አመት የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን በተለይም እንደ ኤሌክትሪሺያን፤ ነርስ፤ የቧንቧ ሰራተኛ፤ የሃኪም ረዳትነት መሰልጠን ለሚፈልጉ የመጨረሻ ዓመት የሃይስኩል ተማሪዎችን ለማገዝ የታቀደ ፕሮግራም ነው።
- The Mary Lou Manzie Memorial Scholarship – ይህ ፕሮግራም በዋናነት የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ከጨረሱ ቢያንስ 3 ዓመት ላለፋቸውና አሁን ተመልሰው አሶሺዬት ዲግሪ ወይም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን መያዝ ለሚፈልጉ ተማሪዎችን ለማገዝ የታቀደ ፕሮግራም ነው።
- The Neil Churchill Memorial Scholarship – ይህ ፕሮግራም በዋናነት የማስተርስ ዲግሪያቸውን (የሁለተኛ ዲግሪያቸውን) መቀጠል የሚሹ አመልካቾችን ለማገዝ የታቀደ ፕሮግራም ነው።
ለሁሉም የስኮላርሺፕ ፕሮግራሞች የተለዩ መመዘኛዎች የተዘጋጁ ሲሆን መመዘኛዎቹን ተመስርቶ እጩዎችና አሸናፊዎች ይለያሉ። ማመልከቻዎችን የማስገቢያ የመጨረሻ ቀን ኤፕሪል 15, 2022 ነው። በመንግስት ድጎማ በሚደረግላቸው የመኖሪያ ቤቶች ነዋሪ ከሆኑ ለእርስዎም ይሁን ለልጆችዎ እድሉ እንዳያመልጥዎ ይህንን ሊንክ ተጭነው ዛሬውኑ ያመልክቱ። ለእርስዎ ካልሆነ ሌሎችን ስለሚጠቅም ለወዳጅ ዘመድ ያጋሩ።