12/12/2024

የፍሬድሪክ ዳግላስ መታሰቢያ ድልድይ የግንባታ ማኔጅመንት ስልጠና ፕሮግራም ምዝገባ ጀመረ። ይህ በዓይነቱ ለየት ያለ ፕሮግራም በኮንስትራክሽን ሙያ ዘርፍ መሰማራት ለሚሹ ለዲሲ-ሜትሮና አካባቢው ነዋሪዎች በተለያዩ የግንባታ ሙያዎች የስልጠና ፕሮግራም ለተመረጡ ግለሰቦች ይሰጣል። ይህ ፕሮግራም ለ8 ሳምንታት የሚቆይ ሲሆን ሰልጣኞች በስልጠና ጊዜ ስራዎቹ ያሉባቸው ቦታዎች ድረስ በመሄድ እየሰሩ የሚማሩባቸው የቲዎሪና የተግባር ፕሮግራሞች አመቻችቷል። ሰልጣኞች በተጨማሪ የኪስ ገንዘብ (አበል) ድጋፍ ይደረግላቸዋል።

በፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ አመልካቾች

  • የሃይስኩል ዲፕሎማ፣ ጂኢዲ ወይም የ10ኛ ክፍል የCASAS or TABE ያለፉ መሆን ይጠበቅባቸዋል
  • ህጋዊ የመንጃ ፍቃድ ሊኖራቸው ይገባል
  • በመግቢያ ምርመራ ወቅትና በስልጠና ላይ እያሉ የአደንዛዥ ዕፅ ምርመራ ማለፍ ይጠበቅባቸዋል
  • በ8 ሳምንቱ ፕሮግራም ሳያቋርጡ መሳተፍ አለባቸው (አበል ይታሰባል)
  • በሳውዝዌስት ዲሲ በሚገኘው የስልጠና ጣቢያና በሜሪላንድና ቨርጂና በተጠሩበት ቦታ በሙሉ ራሳቸውን ችለው መገኘት ይኖርባቸዋል።

የስፕሪንግ ፕሮግራም ከማርች አጋማሽ እስከ ሜይ አጋማሽ ይካሄዳል።

ለማመልከት ሬዙሜዎትን በ cmtp@jsallc.com ይላኩ።

ለበለጠ መረጃ ይህን ይጫኑ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት