12/12/2024

ምንም እንኳን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ቪዥን ዜሮ ግብ በ2030 ከትራፊክ አደጋ ጋር የተገናኙ የሟቾችና የአካል ጉዳተኞች ቁጥር 0 እንደሚሆን ቢያስቀምጥም የእግረኞች ሞት ማሻቀቡን ቀጥሏል። በቅርቡ እንኳን ቅዳሜና እሁድ፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ሶስት እግረኞች በሰዓታት ልዩነት ውስጥ በተሽከርካሪ ለህልፈት ተዳርገዋል።
ከነዚህ ውስጥ አንዱ የ70 አመት አዛውንት የሆኑት አቶ ሞገስ አለምነው ናቸው። አቶ ሞገስ ከሂላንዴል የገበያ ማእከል ፊትለፊት ያለውን መንገድ ሲሻገሩ አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን በቦታው ላይ ተገጭተው ለህልፈት የተዳረጉ 6ተኛ ሰው ናቸው።


እንደ ክሪስቲን ሚንክ (@kristinMink_) ያሉ የማህበረሰብ አንቂዎችና ተሟጋቾች በተደጋጋሚ ቢወተውቱም ምንም ተጨባጭ ለውጥ ባለመደረጉ ምክንያት በተመሳሳይ የእግረኛ መሻገሪያዎች ላይ ነዋሪዎች ለአካል ጉዳትና ለህልፈት እየተዳረጉ ይገኛሉ።

እነዚህ አደጋዎች በአብዛኛው እንደ አውቶቡስ ባሉ የህዝብ መጓጓዣ ተጠቃሚዎች፣ ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑና እና በጥቁሮች ላይ አዘውትሮ የሚታይ በመሆኑ ጉዳዮቹ የፍትሃዊነት መጓደልን ጠቋሚ ያረጋቸዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ታስበው በሎሪግ ቻርኮዲየንና (@lcharkoudian) በጁሊ ፓላኮቪች ካር (@papakovichcarr) የተዘጋጁ ሁለት ረቂቅ ሕጎች በሜሪላንድ ጠቅላላ ጉባኤ ድምፅ እንዲሰጥባቸው የቀረቡ ሲሆን እርስዎም ይህን ሊንክ ተከትለው በመመዝገብ የድርሻዎን መወጣት ይችላሉ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት