phoenix

በፊኒክስ አሪዞና በባነር ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ሴንተር ህክምና እየተደረገለት የነበረው ሰራዊት ገዛኸኝ ደጀኔ የተባለ ኢትዮጵያዊ ጃንዋሪ 29 ከሰዓት 1:21 p.m ላይ ምንነቱ እስካሁን በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት እንዳረፈ የአሜሪካ ኢሚግሬሽንና ድንበር ቁጥጥር መስሪያ ቤት ፌብሯሪ 7 2025 ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ሰራዊት ኦገስት 19 2024 በሉክቪል አሪዞና አቅራቢያ በሜክሲኮ በኩል ድንበር አቋርጦ እንደገባና በወቅቱም በአሜሪካ የድንበር ጠባቂ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ውሎ እንደነበርና በወቅቱም ከአገር እንዲወጣ በባለስልጣናቱ ተፈርዶበት ነበር። ይህንን ውሳኔ ተከትሎም ኦገስት 21 ኢሎይ እስር ቤት ወዳሉት ወደ አይስ (ICE) ኦፌሰሮች ተላልፎ እንደተሰጠና በሴፕቴምበር 20 2024 ዳኛ ፊት ቀርቦ የጥገኝነት ጥያቄውን እንዲያቀርብና ይህ ጉዳዩ እስኪታይለትም እንዳይባረር ተፈርዶለት ነበር።

Ethiopian national in ICE custody passes away at Phoenix-area hospital

በዲሴምበር 20 ሰራዊት በእስር ቤቱ የመዝናኛ ሜዳ ላይ ራሱን ስቶ ወድቆ እንደነበርና በከፍተኛ የልብ መምታትና ድካም ስሜቶች በማሳየቱም ወደ ባነር ካሳ ግራንዴ ሜዲካል ሴንተር ለህክምናና ለምርመራ ተልኮ ነበር። በበንጋታውም ሰራዊት ከሆስፒታል ወደ እስር ቤት የተመለሰ ሲሆን የህክምና ባለሞያዎች ሊምፎማ የተባለ የሊምፍ ካንሰር በሽታ ሳያጠቃው እንዳልቀረ ተናግረዋል። ዲሴምበር 23 ላይ ወደ ባነር ካሳ ግራንዴ ሜዲካል ሴንተር ተመልሶ የገባ ሲሆን በዛም ህክምና እየተደረገለት እስከ ዲሴምበር 31 ቆይቷል።
ዲሴምበር 31 ላይ በአየር አምቡላንስ (ሄሊኮፕተር/አውሮፕላን) ወደ ባነር ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ሴንተር የተወሰደ ሲሆን ከጃንዋሪ 3 ጀምሮ እስከ ህልፈቱ ጃንዋሪ 29መተንፈስ አዳጋች እንዳይሆንበት የመተንፈቻ ቧንቧ ተገጥሞለት ነበር። መረጃውን ያጋራው የአሜሪካ ኢሚግሬሽንና ድንበር ባለስልጣን ጉዳዩን ለቤተሰቦቹ፤ ለኮንግረስና ለሚመለከታቸው ሁሉም አካላት በህጉ መሰረት እንዳሳወቀም አክሎ ገልጿል

የሰራዊት ቤተሰቦች፤ ወዳጅና ጓደኞቹም አስከሬኑን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ የጎፈንድ ሚ አዘጋጅተው የነበረ ሲሆን። ኋላም አስከሬኑን ወደአዲስ አባባ እንደላኩትና ስርዓተ ቀብሩም በአዲስ አበባ ማሕደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደተፈጸመ አስታውቀዋል።

ጎ ፈንድ ሚው ላይ “አቶ ሠራዊት ገዛኸኝ ደጀኔ ከከባድ የስደት ጉዞ በኋላ በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ ገብቶ የነበረ ሲሆን፣ እዚያ ከደረሰ በኋላ በኢሚግሬሽን ቢሮ በሕግ ከለላ ሥር እንዳለ ባደረበት የጠና ህመም ፊኒክስ (አሪዞና) በሚገኘው ባነር ዩኒቨርሲቲ ሜዲካል ሴንተር ለአንድ ወር ያህል በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ45 ዓመቱ ረቡዕ ጥር 21/2017 ዓ.ም. (Jan 29/2025) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል” ሲል ተገልጿል።

Image Credit: Gofundme

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.