tuna

ትራይ ዩኒየን የባህር ምግቦች አምራች ተቋም (Tri-Union Seafoods) የሚያመርታቸውና በ ጄኖቫ (Genova®,)፤ ቫን ካምፕስ (Van Camp’s®)፤ በH-E-B እንዲሁም በትሬደር ጆስ Trader Joe’s የንግድ ስያሜ ለገበያ ያቀረባቸው የቱና ምርቶች በበሽታ አማጭ ባክቴርያ የመበከል እድል ሊኖራቸው ስለሚችል የገዙ ደንበኞች እንዲመልሷቸውና ገንዘባቸውን እንዲወስዱ ጠይቋል።
ይህ ጥሪ የወጣው በቀላሉ የሚከፈቱ የቆርቆሮ ጣሳዎች ላይ ከአምራቾቹ በመጣ ግድፈት በአግባቡ ያልተከደኑ ጣሳዎች መገኘታቸውን ተከትሎ እንዲሁም በጊዜ ሂደት የመከፈት እድላችው ትልቅ መሆኑን ተከትሎ ነው።
ይህም የምርት ግድፈት ቱናውን በክሎስትሪዲየም ቦቱሊነም በተባለና ለህልፈት ሊያበቃ በሚችል ጀርም እንዲበከል ሊያደርገውና ተጠቃሚዎችም በምግብ መመረዝ እንዲጠቁ ሊያደርጋቸው ይችላል ተብሏል። ደንበኞች ጣሳዎቹ ደህና ቢመስሉም፤ ቱናውም ደህና ቢመስል እንኳ ከመጠቀም እንዲቆጠቡ ተመክሯል።
የተበከለ ቱና ተመግበው የታመሙ ሰዎች ደሞ በአፋጣኝ ወደህክምና ቦታ በመሄድ እርዳታ ማግኘት እንደሚገባ በመግለጫው ተጠቅሷል። በዚህ የምርት ግድፈት እስካሁን ድረስ የታመመ ሰው የለም።

ምርቶቹ እስካሁን በሚከተሉት መደብሮች ለሽያጭ ቀርበዋል።

  • H-E-B label – ቴክሳስ
  • Trader Joe’s label – ዴላዌር፤ ኢሊኖይስ፤ ኢንዲያና፤ አዮዋ፤ካንሳስ፤ ኬንታኪ፣ ሜሪላንድ፣ ሚቺጋን፣ ሚኒሶታ፣ ሚዙሪ፣ ነብራስካ፣ ኒው ጀርሲ፣ ኒው ዮርክ፣ ሰሜን ካሮላይና፣ ኦሃዮ፣ ፔንስልቬንያ፣ ቨርጂኒያ፣ ዋሽንግተን ዲሲ እና ዊስኮንሲን
  • Genova 7 oz – በፍሎሪዳና ጆርጂያ ባሉ የኮስኮ መደብሮች
  • Genova 5 oz – ሀሪስ ቲተር፤ ፐብሊክስ፤ H-E-B፤ ክሮገር፤ ሴፍዌይ፤ ዎልማርትና በአላባማ፣ አርካንሳስ፣ አሪዞና፣ ካሊፎርኒያ፣ ፍሎሪዳ፣ ጆርጂያ፣ ሰሜን ካሮላይና፣ ኒው ጀርሲ፣ ቴነሲ እና ቴክሳስ ባሉ ራስ ገዝ መደብሮች።
  • በVan Camp’s ሌብል – ዎልማርትና በፔንሳልቬንያ፤ ፍሎሪዳን ኒው ጀርሲ ባሉ ራስ ገዝ መደብሮች።

በተጨማሪም እንዚህ እንዲመለሱ የተወሰነባቸው ምርቶች የጣሳ መለያ ኮዳቸውና የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜያቸው እንደሚከተለው ነው።

Description UPC Can Code Best if Used By Date 
Genova
Genova Solid White Tuna in Olive Oil 5.0 oz4800000215S94N 42K12/12/2027
S94N 43K12/12/2027
S94N 44K12/12/2027
S94N D1L1/24/2028
Genova Yellowfin Tuna in Olive Oil 5.0 oz4800013265S84N D1N1/13/2028
S84N D2M1/17/2028
Genova Yellowfin Tuna in Olive Oil 5.0 oz 4 Pack4800073265S84N 41M12/13/2027
S84N 42M12/13/2027
S84N 42N12/13/2027
S84N 43N12/13/2027
S84N D1L1/21/2028
S84N D1L1/23/2028
S84N D3L1/24/2028
Genova Yellowfin Tuna in Olive Oil 7.0 oz 6 Pack4800063267S84N D1D1/21/2028
S84N D1D1/23/2028
S84N D3D1/23/2028
S84N D1D1/27/2028
S84N D2D1/27/2028
Genova Yellowfin Tuna in in Extra Virgin Olive Oil with Sea Salt 5.0 oz4800013275S88N D1M1/17/2028
Van Camp’s Seafood
Van Camp’s Solid Light Tuna in Oil 5.0 oz4800025015S83N 45K12/2/2027
Van Camp’s Solid Light Tuna in Oil 5 oz 4 Pack4800075015S83N 45K12/2/2027
Trader Joe’s
Trader Joe’s Solid Light Yellowfin Tuna in Olive Oil51403S74N D2M1/10/2028
Trader Joe’s Solid White Tuna in Olive Oil99287S94N D3N1/13/2028
S94N D4N1/13/2028
Trader Joe’s Solid White Tuna in Water99285S92N D1L1/9/2028
S92N D2L1/9/2028
Trader Joe’s Solid White Water Low Sodium95836S91N 41K12/12/2027
S91N 43M12/13/2027
S91N 44M12/13/2027
 99284S90N D2N1/8/2028
Trader Joe’s Solid White Water No Salt Added S90N D1M1/9/2028
S90N D2N1/9/2028
H-E-B
H-E-B Solid White Tuna in Water 5.0 oz 4 Pack4122043345S9FA 45K12/12/2027
S9FA 46K12/12/2027

መረጃውን ያገኘነው ከ ፌደራል መድኃኒት ባለስልጣን ነው።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.