@ethiopique202 (42)

ቨርጂንያውያን በ2025 ታሪካዊ የሆነውን የገቨርነር ምርጫ በኖቨምበር 4 2025 ያከናውናሉ። ይህ ምርጫ በቨርጂንያ ታሪክ ሁለቱም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሴት እጩዎችን በመወከላቸው የመጀምሪያው ያደርገዋል።

በዴሞክራት በኩል የቀድሞ የሲ አይ ኤ ኦፊሰር የነበሩትና ለ3 ተከታታይ ምርጫዎች ቨርጂንያን በመወከል በኮንግረስ አባል የነበሩትና ለዚህ ውድድር ሲሉ ከኮንግረስ መልቀቂያ አስገብተው የወጡት አቢጌይል ስፓንበርገር የተወከሉ ሲሆን ሪፐብሊካኖች ደግም በአሁኑ ሰዓት በምክትል ገቨርነርነት ከገቨርነር ግሌን ያንግኪን ስር እያገለገሉ የሚገኙትንና የቀድሞ የማሪን ኮር አባል ዊንሰም ኧርል-ሲርስን እጩ አድርገው አቅርበዋል።


የዚህ ምርቻ አሸናፊ የሚሆኑት በቨርጂንያ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ገቨርነር በመሆን ታሪክ ይሰራሉም ተብሏል።

ፌብሯሪ 2025 በሮአኖክ ኮሌጅ በተዘጋጀና 690 ሰዎች በተሳተፉበት የህዝብ መጠይቅ መሰረት የዴሞክራት ወኪል የሆኑት አቢጌይል ስፓንበርገር በ39% ተቀባይነት ሲመሩ የሪፐብሊካን ተወካይ ዊንሰም ኧርል-ሲርስ ደሞ በ24% ይከተላሉ።
ቨርጂንያውያን በአብዛኛው ከአገሪቱ ፕሬዘደንት ተቃራኒ የሆነ ገቨርነር የመምረጥ ባህል አላቸው።

በፕሬዘደንት ትራምፕ የመጀመሪያ ፕሬዘደንትነት ዘመን ቨርጂንያውያን የዴሞክራት እጩ የሆነውን ራልፍ ኖርዛምን የመረጡ ሲሆን ባይደን በ2020 ወደ ስልጣን ሲመጡ ደሞ የአሁኑን የሪፐብሊካን ገቨርነር ግሌን ያንግኪንን መርጠዋል።

አሁን የአገሪቱ ፕሬዘደንት ትራምፕ መሆናቸውን ተከትሎም ይህ ባህል ይቀጥላል ወይንስ ይቀራል የሚለው የሚታይ ይሆናል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.