@ethiopique202 (41)

የቨርጂንያ ገቨርነር ግሌን ያንኪን ኤፕሪል 21 ባወጡት መግለጫ በፌብሯሪ ወር የፕሬዘደንት ትራምፕን ጥሪ ተከትሎ የተቋቋመው የደህንነት ግብረ-ኃይል በቨርጂንያ ሲንቀሳቀሱ ነበር ያላቸውንና ለአገር ደህንነት ስጋት ናቸው ያላቸውን የኤም ኤስ 13ና ትሬን ዴ አራጓ የተደራጁ የውንብድና ቡድኖች ውስጥ በተለያየ የእርከን ደረጃ ውስጥነበሩ ያላቸውን ግለሰቦች መያዙን አስታውቋል

ከተያዙት 521 ሰዎች ውስጥም 132 የነዚህ ቡድኖች አባላት ወይንም ከቡድኖቹጋ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች እንደሆነም አክለዋል።


ይህ ግብረ-ኃይል ከፌደራል ኢሚግሬሽን (አይስ)፤ ከኤፍ ቢ አይ፤ የቨርጂንያ ስቴት ፖሊስና የቨርጂንያ ማረሚያ ቤቶች የተውጣጡ 200 ኦፊሰሮች የተዋቀረ ቡድን ነው።


ይህ ግብረ-ኃይል በቀጣይ ሰነድ አልባና የወንጀል ሬከርድ ያለባቸውን ስደተኞች ለመያዝ ተግቶ እንደሚሰራ ገቨርነር ያንግኪን አስታውቀዋል።


ይህንን ዜና ተከትሎም ሁሉም ቨርጂንያውያን በፖሊሶቻችን ሊኮሩ እንደሚገባም ገቨርነር ያንግኪን ገልጸዋል።

ገቨርነር ያንግኪን በፌብሯሪ 27 ባወጡት ትዕዛዝ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት ይህ ግብረ-ኃይል በማርች 3 ተዋቅሯል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.