@ethiopique202 (38)

በአገር አቀፍ ደረጃ ትልቅ አጀንዳ የነበረውና በርካታ ኢትዮጵያውያንንና ኤርትራውያን በተቃውሞ የተሳተፉበትን የሞንጎምሪ ካውንቲ የትምህርት ከሪኩለምን በተመለከት የወላጆች ክስ በስር ፍርድ ቤቶች ሲንከባለል ቆይቶ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደርሷል።
በዚህ የክስ ሂደት ዋነኛው አጀንዳ የነበረው ወላጆች ከሀይማኖታቸውና ከባህላቸውጋ የሚቃረን ትምህርት ሲኖር ልጆቻቸውን ማስወጣት ይችላሉ ወይስ አይችሉም የሚለው አጀንዳ ነው።
በሞንጎምሪ ካውንቲ ከዚህ ቀደም ወላጆች ልጆቻቸውን ከስርዓተ ጾታ (በተለይም ከተመሳሳይ ጾታ ፍቅርጋ) የተገናኙ ትምህርቶችን ልጆቻቸው እንዳይማሩ የመጠየቅ መብት ነበራቸው።

ሆኖም በ2022 ዓመተ ምህረት የካውንቲው የትምህርት ቦርድ ከዚህ ቀደም በስርዓተ ጾታ ስር ይሰጡ ከነበሩት ትምህርቶች በተጨማሪ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ስር የሚነበቡና የተመሳሳይ ጾታ ጥንዶች ታሪክን የሚዘክሩ የልጆች መጻህፍትን በካሪኩለሙ ውስጥ መካተቱን ተከትሎ ወላጆች ልጆቻቸውን በእነዚህ የትምህርት ክፍሎች እንዳይሳተፉ ሲያደርጉ የከረሙ ሲሆን በ2023 ላይ አዲስ በወጣው የካውንቲው የትምህርት ፖሊስ ግን በእያንዳንዱ መጽሀፍ ንባብ ፕሮግራም ወቅት ተማሪዎች እንዲወጡ ማድረግ አይቻልም በሚል ምክንያት የወላጆችን ከተወሰኑ ትምህርቶች ልጆቻቸውን የማራቅ መብት ከለከለ።

ይህ ውሳኔም በርካታ ወላጆች በተቃውሞ ሰልፍ እንዲወጡና አልፎ ተርፎም በወቅቱ የነበሩትን የካውንቲው የህዝብ ትምህርት ቤቶች ሱፐር ኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ማክናይትና ባልደረቦቻቸውን ወደፍርድ እስከመውሰድ ተደርሶ ነበር። የትምህርት ቦርዱ

በስር ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ይዘው የሄዱት የእስልምና፤ የካቶሊክና የዩክሬን ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወላጆች ታዲያ ልጆቻችንን ከነዚህ የትምህርት አይነቶች ማስወጣት አለመቻል በህገመንግስቱ የተቀመጠውን የሀይማኖት ነጻነት የሚጻረር ነው ሲሉ ከሰዋል። ሆኖም የስር ፍርድ ቤቶች በሁለት ዙር ይህን ክስ ውድቅ ያደረጉት ሲሆን አብዛኛዎቹ ዳኞቹ ወግ አጥባቂ የሆኑት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግን ጉዳዩን ለማየትና የግራ ቀኙን ለመስማት ለዛሬ ማክሰኞ ኤፕሪል 22 ቀጠሮ ይዟል። ይህን ቀጠሮ ተከትሎም በሁለቱም ወገን ያሉ ደጋፊዎች በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በመገኘት ድጋፍና ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ይህ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ በአገር አቀፍ ደረጃ የህዝብ ትምህርት ቤቶችን ሚና የሚወስን ሲሆን በሀይማኖታዊ ነጻነት (religious freedoms)ና በሁሉን አቀፍ ትምህርት (inclusive curricula) መሀከል ያለውን አለመመጣጠን ላይ ውሳኔ እንደሚያሳልፍና ይህም ዘላቂ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ተገምቷል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.