እኛ ስደተኞች እዚህ መጥተን መብታችን ተከብሮልን፤ ሰርተን፤ ተምረን መለውጥ የምንችልበት መንገድ እንዲመቻችልን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የጥቁሮች የመብት ትግል (Civil Rights Movement) ዋነኛው ምክንያት ነው። እነሱ ታግለው የሰው መብት እንዲከበር በማድረጋቸው እንደኛ ያሉ ጥቁር ስደተኞች ተጠቃሚዎች ነን። እንደ ኢትዮጲክ ከማንም በላይ ተሟግተው፤ ተገርፈው፤ በአደባባይ ተገድለው ተስፋ ሳይቆርጡ፤ ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለሌሎች መኖር ምን እንደሆነ አውርተው ሳይሆን ኖረው ያሳዩንን በየዘመኑ የነበሩና አሁንም ያሉ የመብት ተሟጋቾችን እናመሰግናልን። መልካም ጁንቲንዝ።