የሞንጎምሪ ካውንቲ በኮቪድ ምክንያት አቋርጦት የነበረውን አመታዊ የእርሻ ቦታዎች ቱር በዚህ አመት ጀምሮታል። በዚህ ፕሮግራም ላይ በርካታ የእርሻ ቦታዎች፤ የዋይንና ቢራ መጥመቂያዎች፤ የአበባ እርሻ፤ የወተትና የወተት ተዋፆ ማምረቻዎችና የስጋ ግብርናዎች ተካተውበታል።
ማንኛውም ሰው ያለምንም ክፍያ እነዚህን የእርሻ ቦታዎች ዛሬ ጁላይ 23ና ነገ ጁላይ 24 2022 በመሄድ መጎብኘት ይችላል። የእርሻ ምርቶችን ራስዎት ለቅመው መውሰድ ይችላሉ። መልቀሚያዎቹ እዛው ይሸጣሉ። የተወሰኑት ቦታዎች እዛው እርሻው ቦታ ላይ የምግብና መጠጥ አገልግሎት ይሰጣሉ።
የእርሻዎቹን ዝርዝር አድራሻ ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጫኑ።
የካውንቲውን አስረጂ መረጃ ከነማፑ ለማግኘት ይህን ይጫኑ።