12/12/2024
Untitled design (6)

ታይታኒየም ዳዮክሳይድ የተባለውን ኬሚካል በስኪትልስ ቸኮሌት ካንዲ ውስጥ በመጠቀሙ ምክንያት የቸኮሌት ካንዲዎቹ አምራች የሆነው ማርስ ካሊፎርኒያ በሚኖርና ጄኒል ቴምስ በተባለ ደንበኛው ክስ ቀርቦበታል።
ከሳሽ እንደሚለው አምራቹ ለስኪትልስ ማቅለሚያነት የሚጠቀመውን የታይታኒየም ዳዮክሳይድን ጉዳት ለደንበኞቹ ማሳወቅ አለበት ብሏል።
አምራቹ በበኩሉ የደንበኞቻችንንን ደህንነት ከምንም በላይ ያሳስበናል። ይህንን ተከትሎም በህግ ያልተፈቀዱ ኬሚካሎችን አንጠቀምም። ታይታኒየም ዳይኦክሳይድም በጣም በርካታ ለሆኑ ምርቶች በግብዓትነት ያገለግላል የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣንም ኬሚካሉን ለመጠቀም ባስቀመጠው መጠን ልክ እንጠቀማለን ሲሉ ምላሽ ሰተዋል።
የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አምራቾች ኬሚካሉን ከ 1% ባልበለጠ መጠን እንዲጠቀሙ ያስገድዳል። ኬሚካሉ በአውሮፓ ከ2021 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ክልክል ነው።
ታይታኒየም ዳይኦክሳይድ በዋናነት በሰውነት በአግባቡ የማይወገድ መሆኑና የመከማቸት ባህሪ ስላለው ለጤና ጠንቅ የምሆን እድሉ ትልቅ እንደሆነ የኬሚካል ኢንጂነር የሆኑት ቶም ኔትነር ለዔንፒአር (NPR) አስታውቀዋል። በተጨማሪም ባለሞያው ይህ ኬሚካል በሰውነት ውስጥ ሲከማች የሰዎችን ዲ ኤን ኤ በማዛባት እንደ ካንሰር ላሉ በሽታዎች ሊያጋልጥ እንደሚችል ጠቁመዋል።
ዘገባው የዔንፒአር (NPR) ነው።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት