12/12/2024
Untitled design (7)

ከ7-12ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑ የታኮማ ፓርክ ከተማ ነዋሪ ታዳጊዎች በከተማው ካውንስልነት እንዲያገለግሉ ጥሪ ቀረበ።

ይህ የታዳጊዎች ካውንስል ለአባላቱ የመንግስን አሰራር በቅርበት እንዲያውቁ ያግዛል ተብሏል። በተጨማሪም አባላቱ የከተማዋን ታዳጊዎች ወክለው ችግሮቻቸው ላይ ይመክራሉ በዚያውም የመሪነት ክህሎትን እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል።

የታዳጊዎች ካውንስል አባላት ከተመረጡ በኋላ ለአንድ አመት ያገለግላሉ። ተሳታፊዎች እስከ 40$ አበል የሚከፈላቸው ሲሆን በስብሰባዎች ተገኝተው ያሳለፉት ሰዓታት ወደ SSL ይቀየርላቸዋል።

የማመልከቻው የመጨረሻ ቀን ሴፕቴምበር 7 ነው። ለበለጠ መረጃ ከስር ባሉት አድራሻዎች መጠየቅ ይችላሉ።

ለማመልከት ይህን ሊንክ ተከትለው ይሂዱ።

Contact Jessie Carpenter, 301-891-7267 or email jessiec@takomaparkmd.gov.

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት