የዲሲ ፖሊስ ፋኑኤል ሰለሞን የተባለ የ30 ዓመት ወጣት ያለበትን የምታውቁ ጠቁሙኝ ብሏል። ፋኑዔል ለመጨረሻ ጊዜ የታየው ዛሬ ሰኞ ሜይ 8 2023 በ3500 14th ST NW ጥቁር አንበሳ መደብር አካባቢ ነው። ፋኑኤል ቀመቱ 5’3” ጥቁር ፀጉር ና ቡናማ የአይን ቀለም አለው። ለመጨረሻ ጊዜ ጥቁር ጃኬትና ጥቁር ሱሪ አርጎ ነው የወጣው። ፋኑዔል ምናልባትም የሚወስደውን መድኃኒት ሳይዝ የወጣ በመሆኑ ፖሊስ ያለበትን የምታውቁ ጠቁሙኝ ብሏል። ያለበትን የምታውቁ በ ስልክ ቁጥር 202-727-9099 በመደወል ወይንም በ 50411 ቴክስ በመላክ ማሳወቅ ትችላላችሁ። ይህን መልዕክት ሼር በማድረግም ማገዝ ይቻላል።