12/12/2024
ከአጋዘንጋ በተጋጨ መኪና የሰው ህይወት አለፈ

ከትላንት በስትያ ረቡዕ ሜይ 17 2023 ከምሽቱ 8፡30 ገደማ ወደ በደለስ አክሰስ ሃይዌይ ላይ ወደ ደለስ ኤርፖርት ተሳፋሪ ጭኖ በመጓዝ ላይ ሳለ ከአጋዘን (deer) ጋር ተጋጭቶ የሹፌሩ ህይወት ወዲያው ሲያልፍ ተሳፋሪው ደግሞ ጉዳት ደርሶበት ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።
በዚሁ አደጋ ምክንያተም መንገዱ ለ4ሰዓታት ያህል ተዘግቶ ነበር።

ፖሊስ የሟችን ማንነት እስካሁን አላስታወቀም ሆኖም የሟች ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ራኬብ ገብረማርያምና ወንድማቸው አቶ ቴዎድሮስ ገብረማርያም ለቀብር ማስፈጸሚያ በከፈቱት ጎፈንድ ሚ ገጽ ላይ ሟቹ ሰለሞን ብርሀኔ ስብሀቱ እንደሆነ ታውቋል። አቶ ሰለሞን ባለትዳርና የሁለት ታዳጊ ወንድ ልጆች አባት ሲሆን በሜሪላንድ ሲልቨር ስፕሪንግ ነዋሪም ነበር።

ቤተሰባቸውን መርዳት ለምትፈልጉ ይህን ሊንክ በመጫን መለገስ ትችላላችሁ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት