05/18/2024

ኮምካስት ራይዝ ኢንቨስትመንት ፈንድ 

ማመልከቻው ከኦክቶበር 1-14 ለዋሽንግተን ዲሲ ነጋዴዎች ክፍት ይሆናል 

ኮምካስት በወርሃ ሰኔ፣2020 ዓ.ም. እንዳስታወቀው ለተከታታይ ዓመታት የሚዘልቅ የ75 ሚሊዮን ዶላር የካሽና የ25 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ የሚዲያ ድጋፍ ኢፍትሃዊነትን ለመግታት፤ የዘር መድልዖንና የመሳሰሉትን የማይታዩ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን ለመታገል ኮምካስት ራይዝ ኢንቨስትመንት ፈንድ 

የተባለ ፕሮጀክት ተገባራዊ አድርጓል።  

በዚህም ፕሮጀክት የውድድሩን መስፈርት የሚያሟሉ በዋሽንግተን ዲሲ፤ ሂውስተን ቴክሳስ፤ ማያሚ ፍሎሪዳ፤ ሚኒያፖሊስ-ሴይንት ፖል ሚኔሶታ፤ ኦክላንድ ካሊፎርኒያ፤ እና ሲያትል ዋሽንግተን ያሉ የንግድ ተቋማት መወዳደር ይችላሉ።  

በዚህ ውድድር  

  • ለ600 አሸናፊ ድርጅቶች በጠቅላላው 6ሚሊዮን ዶላር ይሰጣል 
    • በእያንዳንዱ ከተማ 100 አነስተኛ የንግድ ተቋማት ይሸለማሉ 
    • ሁሉም አሸናፊዎች እያንዳንዳቸው 10ሺህ ዶላር ይሸለማሉ 
  • የማመልከቻ ጊዜ  ከኦክቶበር 1-14 2021 
    • በኖቬምበር መጨረሻ የውድድሩ አሸናፊዎች ውጤት ይፋ ይደረጋል።  

በውድድሩ ማን መሳተፍ ይችላል? 

  • ከተቋቋሙ 3ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው የንግድ ድርጅቶች። 
  • በስራቸው ከ25 ያልበለጡ ቋሚና የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ያሏቸው ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ 

በዚህ ውድድር ለመሳተፍ ይህን ይጫኑ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት