12/12/2024
የሊሞ ሹፌር የሆነው ሚካኤል ጽጌ ድብደባና ዝርፊያ በዲሲ (6)

UPDATE: የዲሲ ፖሊስ አቶ ተስፋሚካኤል ገብረመስቀል በሰላም እንደተገኙ በትዊተር ገጹ አስታውቋል።

የዲሲ ፖሊስ ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው የአፋልጉኝ ጥሪ ተስፋሚካኤል ገብረመስቀል የተባሉ የ76 አመት አዛውንት ያሉበትን የሚያውቅ ወይንም ያያቸው ሰው እንዲጠቁም ጥሪ አቅርቧል። አቶ ተስፋሚካኤል ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት ትላንት ቅዳሜ ጁን 17 2023 በ 2800 block Otis st NE አካባቢ ከምሽቱ 8፡30 ገደማ ነው ተብሏል።
አቶ ተስፋሚካኤል ገብረመስቀል ቁመታቸ 5’7’’ ክብደታቸው 150 ፓውንድ ሲሆን ሽበት ያለበት ጥቁር ጸጉርና ቡናማ የዓይን ቀለም አላቸው ተብሏል። በወቅቱ የለበሱት ልብስ የማይታውቅ ከመሆኑም በላይ መድኃኒታቸውን መውሰድ እንዳለባቸውም ተጠቁሟል። የአቶ ተስፋሚካኤልን መገኛ የሚያውቅ ወይንም ያያቸው ሰው ለዲሲ ፖሊስ በስልክ ቁጥር 202-727-9099 ወይንም በ202-576-6768 በመደወል ወይንም በ 50411 ቴክስት በመላክ መጠቆም እንደሚቻል ተነግሯል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት