UPDATE: – ቅዱስ ወገን እንደተገኘ የአርሊንግተን ፖሊስ አስታውቋል።
የአርሊንግተን ካውንቲ ፖሊስ ዛሬ ባወጣው የአፋልጉኝ ማስታወቂያ ቅዱስ ወገን የተባለ የ16 ዓመት ታዳጊ ያለበትን የምታውቁ ጠቁሙኝ ብሏል። ቅዱስ ቁመቱ 5’10” ሲሆን ክብደቱ ደሞ 170 ፓውንድ እንደሆነ ተጠቁሟል። ቅዱስ ለመጨረሻ ጊዜ የታየው በ1300 block of S. Glebe Rd ሲሆን በወቅቱ ቀይ ጃኬት፤ ጥቁር ከናቴራ/Shirt፤ ጥቁር ጂንስ ሱሪና ጥቁር ጫማ ተጫምቶ ነበር ተብሏል።
የቅዱስን መገኛ የሚያውቅ ወይንም መረጀው ያለው ማንኛውም ሰው በስልክ ቁጥር 703-558-2222 ወይንም በ 911 በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል ተገልጿል።