12/12/2024
We are proud of you (1)

በፕሪንስ ዊልያም ካውንቲ የሚገኘው የፓትሪዮት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሁለት ተማሪዎቹ ትወክሎ በቨርጂንያ ሀይስኩል ሊግ (Virginia High School League (VHSL)) የተወዳደረ ሲሆን ከመላው ቨርጂንያ አንደኛ በመውጣት አሸንፏል። ለዚህ ስኬት ያበቁት ሁለት ተማሪዎች የትምህርት ቤቱ ሲንየር የሆኑት ጃክ ሜዶር እና አቤኔዘር ፍታው ናቸው።
አቤኔዘር ፍታው ለምን በክርክር መወዳደር እንደፈለገ ሲጠየቅም የንግግር ክህሎቱን ለማዳበር በተለይም ህዝብ ፊት ቆሞ የመናገር ፍርኃቱን ለማስወገድ እንዲሁም ስለአንድ ጉዳይ ጠለቅ ያለ ምርምር ማድረግን እንደሚማርበትና ይህ የክርክር መድረክም ወደፊት በኮሌጅና በቀሪው ህይወቱ ለሚጠበቅበት ሁሉ ዝግጁ እንዲሆን መሰረት እንደጣለለት ተናግሯል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት