በ2016 የ22 ዓመት ወጣት የሆኑትን ሄኖክ ዮኃንስንና ቅድስት ስሜነህን ገድሎ ወደኢትዮጵያ ሸሽቶ ለ3 አመት ተደብቆ ከቆየ በኋላ ከኢትዮጵያ ዲፖርት ተደርጎ ወደዚሁ አሜሪካ የመጣውን ዮኃንስ ነሲቡን የፌርፋክስ ካውንቲ ጁሪ በያዝነው አመት መጀመሪያ አካባቢ ጥፋተኛ እንደሆነ ብይን ሰጥቶበት ነበር።
ዳኛው ለ28 ዓመት ወጣቱ ዮኃንስ ነሲቡ ዛሬ የዕድሜ ይፍታህ ብይን ሲስጡ ታዲያ ዮኃንስ ዳኛውንና የሟች ቤተሰቦችን ድምጹን ከፍ አርጎ ደጋግሞ ፋክዩ እያለ በአስነዋሪ ስድብ ሲሳደብ እንደነበር በፍርድ ቤቱ የታደሙ የwusa9 ጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ለጥቆማው ሆሳዕና ምህረቱን እናመሰግናለን።