ሞንጎምሪ ካውንቲ ፖሊስ ተፈላጊዎቹ በሰላም በጤና መገኘታቸውን አስታውቋል
———————————–
UPDATE: Emebet Asfaw Mengistu, Rakeb Wudneh and Meklit Wudneh have been located safe and unharmed.
የሞንጎምሪ ካውንቲ ፖሊስ 3ኛ ዲስትሪክት ዛሬ ማምሻውን ባወጣው የአፋልጉኝ ማስታወቂያ የ34 አመቷ እመቤት አስፋው መንግስቱንና የ2 አመቷ ራኬብ ዉድነህ እንዲሁም የ 10 ወር እድሜ ያላት መክሊት ውድነህ ያሉበትን የሚያውቅ ይጠቁመን ብሏል።
ዛሬ ረቡዕ ጁን 14 2023 ከጠዋቱ 8፡30 እመቤት፤ ራኬብና መክሊት ለመጨረሻ ጊዜ በ8600 ብሎክ 16th Street in Silver Spring አካባቢ ታይተዋል ብሏል ፖሊስ።
እመቤት ምናልባትም የሜሪላንድ ታርጋ ያለውና የታርጋ ቁጥሩ 2ET5079 የሆነ የ2018 ቶዮታ ራቭ4 እያሽከረከረች ሊሆን እንደሚችል ፖሊስ አስታውቋል።
እመቤት 5 ጫማ ከ 5 ኢንች ስትሆን 126 ፓውንድ ትመዝናለች ሲል ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።
ፖሊስ አክሎም ራኬብ 28 ፓውንድና ባለ ቡናማ ጸጉርና ቡናም አይን እንዲሁም መክሊት 20 ፓውንድና ጥቁር ጸጉርና ቡናማ አይን እንዳላቸው ገልጿል።
ቤተሰቦቻቸው እንደተጨነቁና ያሉበትን የሚያውቅ በስልክ ቁጥር 303-279-8000 ደውሎ ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቋል።