12/12/2024
የሊሞ ሹፌር የሆነው ሚካኤል ጽጌ ድብደባና ዝርፊያ በዲሲ (1)

በዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ የፉድ ስታምፕ ላላቸው ነዋሪዎች የባስና የባቡር ዋጋ በግማሽ ቅናሽ እንደሚያደርግ ሜትሮ አስታውቋል። ማንኛውም ፉድ ስታምፕ የሚቀበል ነዋሪ ከመጪው ማክሰኞ ጀምሮ ኦንላየን ወይንም በአካል ወይንም በፖስታ ቤት በማመልከት የዚህ ቅናሽ ተጠቃሚ መሆን ይችላል።

በአካል ተገኝቶ ለማመልከት ከሚከተሉት ቦታዎች በአንዱ ከማክሰኞ ጁን 20 ጀምሮ በመሄድ ማመልከት ይቻላል።

– Metro Center Metro Station፣ 12th & F Street NW – Mezzanine Level

– Metro Headquarter፣ 300 7th Street SW, Washington, DC 20024

New Carrollton Metro Offices፣ 4100 Garden City Dr, Hyattsville, MD 20785

ለማመልከት ሲሄዱ ቀኑ ያላለፈ መታወቂያ፤ የባስ/ሜትሮ ካርድ፤ የኢቢቲ ካርድ (ለቤተሰብ አባላት የሚያመለክቱ ከሆነ የቤተሰብ አባላቱ ስም ያለበት የኢቢቲ ፍቃድ ወረቀት)፤ እንዲሁም የስልክ ቁጥርዎን ይዘው መሄድዎን አይርሱ።

ለበለጠ መረጃ ይህን ይጫኑ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት