12/12/2024
የሊሞ ሹፌር የሆነው ሚካኤል ጽጌ ድብደባና ዝርፊያ በዲሲ

የአርሊንግተን ነዋሪ የሆነውና በሊሞ ሹፍርና ስራ ላይ የተሰማራው ሚካኤል ጽጌ ከሰሞኑ የድብድባና የመኪና ዝርፊያ ሰለባ ሆኗል፡፡

ሚካኤልም ስለጉዳዩ ለጠየቀው የኤንቢሲ ጋዜጠኛ ሲያስረዳ “አንደኛውን ሰውዬ እያናገርኩ ሌላኛው በተሳፋሪ በኩል መቶ የመኪናውን መስታወድ በዲንጋይ ሰበረው እኔም ምን እንደተፈጠረ ለማየት ስዞር አጠገቤ የነበረው እየደበደበ ከመኪናው ጎትቶ ለማውረድ ሞከረ”

Source: NBC4

“ሌቦቹ መኪናው ውስጥ ገብተው ሲሄዱ ታዲያ የሚካኤል እግር በሲትቤልቱ ይተበተብና ይያዛል እነሱም ሚካኤልን መሬት ለመሬት እየጎተቱ መኪናውን ይዘው ሄዱ፡፡

መኪናው የት እንዳለ ማሳወቂያ ያለው ሲሆን ሚካኤልም ያለበትን ቦታ ለፖሊስ ቢነግርም አስፈላጊውን ትብብር እያገኘ እንዳልሆነ አስረድቷል፡፡

ፖሊስ በበኩሉ ምርመራ እያደረገ እንደሆነና የተጠርጣሪዎቹ ማንነት የሚያሳይ ምስል በትዊተር ገፁ አውጥቷል::

ሚካኤል እስኪሻለውና ስራ እስኪጀምር ጊዜ እንደሚወስድበት ተናግሯል፡፡

ዜናውን ያገኘነው ከኤንቢሲ4 ነው፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት