12/12/2024
Screenshot 2023-07-12 at 21.19.56

ከወይዘሮ ሰብለና ከአቶ ግርማ የተገኘችው ኢትዮ-አሜሪካዊቷና ለሴቶች የሶከር ብሄራዊ ቡድን በተከላካይነት የምትጫወተው የ23 አመቷ ናኦሚ ግርማ ለስደተኛ ልጆች ድጋፍና እርዳታ ከመጠየቅ ወደኋላ አትበሉ ብላለች:: ናኦሚ የመጀመሪያ የእግርኳስ ልምምዷንና ጨዋታዋን የጀመረችው ከሳንሆዜው ማለዳ ክለብ ጋር እንደሆነም ከሶከር ዳት ካም ጋር ባደረገችው ቃለ መጠይቅ ገልጻለች፡፡

ምንጭ፡ soccer.com ለጥቆማው Hosanna Meheretuን እናመሰግናለን

ናኦሚ የአሜሪካን የሴቶች የእግር ኳስ ቡድንን ወክላ በመጪው የፊፋ የሴቶች የአለም ዋንጫ ላይ ትሳተፋለች። ናኦሚ እድገቷ ሳን ሆዜ ካሊፎርኒያ ሲሆን አሁን በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ለሳንዲዬጎ ዌቭ San Diego Wave FC ክለብ ትጫወታለች። ከሰሞኑም ከኤንቢሲ ጋር ያደረገችውም ቃለ መጠይቅ ለማዳመጥ ፕሌይን ይጫኑ

በአሁኑ ሰዓትም በማኔጅመንት ሳይንስና ኢንጂነሪንግ ማስተርሷን ለመጨረስ እየሰራች ነው።

የናኦሚን ሙሉ ታሪክ ለማንበብ ሊንኩን ተከትለው ይሂዱ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት