12/12/2024

የዲሲ ፖሊስ ዛሬ ሐሙስ 08/17 እንዳስታወቀው ከዛሬ ጀምሮ እድሜያቸው ከ17 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችን ከእሁድ እስከ ሐሙስ ከምሽቱ 11 ሰዓት በኋላይህ አርብና ቅዳሜ ደሞ ከእኩለ ለሊት በኋላ ያገኛቸውን ታዳጊዎች ወደ ማቆያ ጣቢያ በመውሰድ የምክርና ማገገሚያ አገልግሎት እንዲያገኙና ከወላጆቻቸውጋር እንዲገናኙ የማድረግ ስራ ሊጀምር እንደሆነ አስታውቋል።

የዲሲ ፖሊስ ቺፍ በተለይም ዘንድሮ ወንጀል ከአምናው በ38%ማደጉን ተከትሎ የተለያዩ እርምጃዎችን እንደሚወስዱና በተለይም የታዳጊዎች በወንጀል ተሳታፊነት መበራከትን ለመቀልበስ ይህን የሰዓት እላፊ ፕሮግራም እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል። በ1995 በወጣው የዲሲ ህግ መሰረት ማንኛውም እድሜው ከ17 በታች የሆነ ታዳጊ ከምሽት 11 ሰዓት በኋላ ከብቤት ውጪ መገኘትን ይከለክላል።

ይህ ቁጥጥር ተግባራዊ የሚሆንባቸው ሰፈሮችም በዋናነት እኚሁ ታዳጊ ጎረምሶች ያዘወትሯቸዋል የተባሉት ቻይናታውን፤ ኔቪ ያርድ፤ ዩ ስትሪት አካባቢ፤ ኃዋርድ ዩኒቨርስቲ አካባቢ፤ ባነከር የመዝናኛ ማዕከል፤ 14ዝ ስትሪት በኦቲስና ስፕሪንግ ሮድ መኃል፤ 4000 block of Georgia Avenue NW; the 4400-4600 block of Benning Road SE; and the 1300 block of Congress Street SE ናቸው።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት