12/12/2024
መልካም ኦክቶበር ይሁንላችሁ!! (3)

ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ “Ethiopia at the Crossroads” የሚል ስያሜ የተሰጠው የኢትዮጵያን የ1750 አመት ታሪክ ከዘመናዊ የስነጥበብ ስራዎችጋ የሚቃኝ የስነጥበብ አውደ-ርዕይ በዎልተር የስነጥበብ ሙዚየም ከዲሴምበር 3 2023 እስከ ማርች 3 2024 ለህዝብ ክፍት ይሆናል።

ይህ አውደ-ርዕይ የኢትዮጵያ ስነጥበብ ታሪካዊ አንድምታን የሚቃኝ ሲሆን ኢትዮጵያ በአለም መድረክ ላይ የነበራትን ኃይማኖታዊ፤ ባህላዊና ሰብዓዊ መስተጋብሮችን ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች በየዘመናቸው የገለጹበትና ከሌሎች ሀገራትጋ የነበራቸውን መስተጋብር ያሳያል ተብሏል። የአውደ-ርዕዩ አዘጋጆች ከኢትዮጲክ ባልደረባ ከሔኖክ ጋር በነበራቸው ቆይታ ከ220 በላይ ቅርሶችና የስነጥበብ ቁሶች ለዕይታ እንደሚቀርቡ አስረድተዋል። ከስር ባለው ቪድዮ ሙሉ ቃለመጠይቁን ይመልከቱ።

በዚህ አውደ-ርዕይ ል አይ በተጨማሪም የዘመናችን የስነጥበብ ባለሞያ የሆኑት እነ ወሰነወርቅ ኮስሮፍና አይዳ ሙሉነህን የመሳሰሉ አርቲስቶች ስራዎች ለዕይታ ይቀርባሉ። ይህ አውደ-ረዕይ በ ዎልተርስ አርት ሙዚየም፤ በፒበዲ ኢሴክስ ሙዚየምና በቶሌዶ ሙዚየም ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን ቅርሶቹና የስነጥበብ ስራዎቹ በኤፕሪል ወር 2024 ወደ ኢሴክስ በኦገስት 2024 ደሞ ወደቶሌዶ በመሄድ ለእይታ ይቀርባሉ። በዚህ አውደ-ርዕይ ላይ ከስነጥበባዊ ስራዎች ባሻገር በርካታ ፕሮግራሞች ለታዳጊዎችም ለአዋቂዎችም ተዘጋጅቷል።

ይህን አውደርዕይ ማንኛውም ሰው ከዲሴምበር 3 ጀምሮ በ 600 N Charles St, Baltimore, MD 21201 በመገኘት በነጻ ሊጎበኘው እንደሚችል የዎልተር የስነጥበብ ሙዚየም የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ሲድኒ አዳምሰን ለኢትዮጲክ ተናግረዋል።

ለመረጃው አባይ ገብሬን እናመሰግናለን።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት