ጋልቭስተን ስትሪት በሳውዝ ዌስት ዲሲ የ3አመት ህፃን ቤት ውስጥ በአግባቡ ሳይቆለፍበት የተቀመጠ ሽጉጥ አግኝቶ የአምስት አመት እህቱ ላይ በመተኮስ አቁስሏታል:: ተጎጂዋ ህፃን በእርዳታ ሰራተኞች ወደሆስፒታል ተልካለች::
ፖሊስ ተጠርጣሪ ያለውን የህፃናቱ ወላጆች ጏደኛን በቁጥጥር ስር አውሎታል:: ይህ ሰው የልጆቹ እናት ገበያ በሄደችበት ወቅት ልጆቹን ለመጠበቅ የመጣ ሰው እንደሆነ ፖሊስ አስታውቋል::