@ethiopique202 (16)

በቨርጂኒያ ግዛት የፍሬድሪክስበርግ ባለሥልጣናት ትላንት ማክሰኞ እንዳስታወቁት፤ ስፖጽልቬንያ ካውንቲ ፍሬድሪክ ከተማ በተፈጸመ ተኩስ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ በትንሹ ሌሎች  ሦስት ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸው  “ሁሉም ተጠርጣሪዎች” በቁጥጥር ስር እንደዋሉ አስታውቀዋል። 

ሁለት የ16 ዓመት ታዳጊዎች፣ አንድ የ17 ዓመት ታዳጊ እና ጀርማያ አፕሰን የተሰኘ የ18 ዓመት ወጣት በቁጥጥር ስር ውለው “ተደራጅተው መሳሪያ በመጠቀም ከባድ ጉዳት በማድረስ እና  ህገወጥ ድርጊት በመፈጸም” በሚል መከሰሳቸውን ፖሊስ ዛሬ  ረቡዕ ማለዳ ባሰራጨው መረጃ አመልክቷል። 

ይህ የወንጀል ተግባር ትላንት አመሻሽ 5:30 አካባቢ መፈጸሙን ፖሊስ መረጃው እንደደረሰው አስታዉቋል። በቦታው ከነበሩትና አደጋው ከደረሰባቸው ስድስት ሰዎች መካከል ሦስቱ ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ብለዋል ። በጥቃቱ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉም በሰዓቱ ተገልጿል። 

አደጋው የደረሰው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሊገበያዩ የነበሩ ሰዎችን ለመዝረፍ በተደረገ ሙከራ ሳይሆን እንዳልቀረ ተጠርጥሯል፡፡ አደጋውን ተከትሎ የፍሬድሪክስበርግ ከተማ የህዝብ ትምህርት ቤቶች በ2 ሰዓት ዘግይተው ትምህርት እንዲጀምሩ ተደርጓል፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.