@ethiopique202 (17)

ቻይና ከነገ ሀሙስ ጀምሮ በአሜሪካ ምርቶች ላይ 84 ከመቶ ታሪፍ መጣሏን በማስታወቋ፤ ከአሜሪካ ጋር በተባባሰ የንግድ ጦርነት ውስጥ የገባች ሲሆን፤ ”እስከ መጨረሻው ለመታገል” ቃል መግባቷን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል ።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ አጠቃላይ ታሪፉን ወደ 104 በመቶ ከፍ ካደረጉ በኋላ ቤጂንግ በርካታ የመከላከያ እርምጃዎችን ወስዳለች። 

ቤጂንግ በዓለም ንግድ ድርጅት ውስጥ በአሜሪካ ላይ ተጨማሪ አዲስ ክስ እየመሰረተች ያስታወቀች ሲሆን፤ በተጨማሪም ከቻይና ኩባንያዎች ጋር የንግድ ልውውጥ ባላቸው የአሜሪካ ኩባንያዎች ላይ ተጨማሪ ገደቦችን እንዳስቀመጠች አስታውቃለች።

ይሁን እንጂ ቻይና ሌሎች የዓለም መንግስታት እያደረጉ እንዳሉት ከዋይት ኃውስ ጋር እየተደራደረች እንደሆነ ከማስታወቅ ተቆጥባለች። 

ቻይና ባለፈው ሳምንት አርብ ነበር አሜሪካ ለጣለችባት ታሪፍ ተመጣጣኝ ነው ያላቸውን 34 ከመቶ ታሪፍ መጣሏን ያስታወቀችው። ይህን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቻይና ላይ የተጣለውን ታሪፍ ወደ 50 ከመቶ ያሳደጉት ሲሆን ከቻይና ጋር ድርድር አያስፈልግም በማለት ድርድሩን አቋርጠዋል።

እስካሁን ድረስ ባለው የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን እረቡ ዕለት እንዳሉት “ዩናይትድ ስቴትስ ጉዳዮችን በውይይት እና በድርድር ለመፍታት በእውነት ከፈለገች የእኩልነት፣ የመከባበር እና የጋራ ተጠቃሚነትን አስተሳሰብ ማዳበር አለባት” በማለት ለድርድር እምብዛም ፍላጎት እንደሌላት ጠቁመዋል። 

ይህንን እሰጥ አገባ ተከትሎም ፕሬዘደንት ትራምፕ በቻይና ላይ የጣሉትን የታሪፍ መጠን ወደ 125% እንዳሳደጉትና በሌሎች አገራት ላይ የጣሉትን ታሪፍ ኝ ለ90 ቀናት እንደሚያዘገዩ በትሩዝ ሶሻል አካውንታቸው አስታውቀዋል፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.