
የፌደራል አስቸኳይ ይግባኝ ለመስማት ከሰሞኑ ቀጠሮ ይዞ የነበረው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ መንግስት በስህተት ዲፖርት ያደረገውን ሰው እንዲመልስ ውሳኔውን አስተላልፏል።
አብሬጎ ኮሌጅ ፓርክ አቅራቢያ ከታሰረ በኋላ ወደ ባልቲሞር ማቆያ ጣቢያ እንደሄደና ቀጥሎ ወደ ሉዊዚያናና፤ ቴክሳስ አድርጎ ኤልሳልቫዶር ወደሚገኘው ወደ ቼንትሮ ኮንፋይንመንቶ ደል ቴሮሪዝሞ ወደተባለው አስከፊ እስር ቤት ዲፖርት ተደርጎ የነበረ ሲሆን አይስ (ICE) ወደ ኤልሳልቫዶር ዲፖርት ያደረገው የቬንዙዌላ ዜጋ ስደተኛ በስህተት እንደሆነና በአስተዳደራዊ ግድፈት ምክንያት ይህ ሊፈጠር እንደቻለ አስታውቆ ነበር።
ኪልማር አብሬጎ ጋርሲያ የተባለ የ29 ዓመት ወጣት በስህተት በመንግስት አካላት ታስሮ ማርች 15 ወደ ኤልሳልቫዶር ከተላከ በሁዋላ በአስከፊው የማጎርያ ካምፕ እንደገባ ተነግሯል።
ይህንን ተከትሎም ወቀሳ የቀረበበት ዋይት ኃውስ በፕሬስ ሴክሬተሪ ካሮሊን ሌቪት በኩል “ይህ የተፈጠረው በአስተዳደራዊ ስህተት ነው።
ይህም ቢሆን ግን የትራምፕ አስተዳደር ይህ ወደ ኤልሳልቫዶር ዲፖርት የተደረገ ግለሰብ የኤም ኤስ 13 የተደራጀ የወንጀል ቡድን አባል እንደሆነ በቂ መረጃ እንዳላቸውና በፍጹም ወደ አሜሪካ እንደማይመጣና አልፎ ተርፎም ይኸው ሰው በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሳትፎ እንደነበረው በቂ መረጃ አለን” ብለው ነበር።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኪልማር እንዲመለስ ያዘዙትን ዳኛ የወሰኑት የቀነ ገደብ ሰኞ ለሊት በማለፉ ትእዛዛቸውን እንዲያድሱና በግልጽ እንዲያስቀምጡ ያዘዘ ሲሆን መንግስ ደሞ እስካሁን ምን እርምጃዎችን እንደወሰደና ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ ምን ቀሪ ተግባራት እንደሚቀሩት እንዲያሳውቅ አዘዋል።
የሱፕሪም ኮርት ውሳኔ በቀታይ ያሉ የስደተኞች ውሳኔዎች ላይም እንደማመሳከሪያ ሆኖ የሚቀርብ በመሆኑ ለስደተኞች እፎይታ ሆኗል።