
የሜትሮፖሊታን አካባቢ ሬስቶራንት አሶሴሽን በሰዋና ከ200 በላይ የሬስቶራንት ባለቤቶች ተሳትፈውበታል በተባለበት ጥናት 47% የሚሆኑት በ2024 የደንበኞቻቸው ቁጥር እንደቀነሰ ያስታወቁ ሲሆን 44% የሚሆኑት ገበያው ያንሰራራል የሚል ተስፋ እንደሌላቸውና በ2025 ሬስቶራንታቸውን ሊዘጉ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
ባለፉት ሦስት ወራት በከፍተኛ ሁኔታ ከስራ እየተቀነሱ ባሉ የፌድራል ሰራተኞች ምክንያት በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚገኙ ምግብ ቤቶች ገበያቸው እየተቀዛቀዘ መሆኑን ተናገሩ።
በዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ የሚገኙ የንግድ ቤት ባለቤቶች እና የንግድ ማኅበረሰቦች ፤ በጉዳዩ ላይ ከዋሺንግተን ዲሲ የመንግስት ምክር ቤት ጋር፤ ትላንት ረቡዕ ተነጋግረዋል።
በተለይም በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ሆቴሎች፤ የፌድራል ሰራተኞች ከሥራ በመቀነሳቸው እንዲሁም ተያያዥ የሆኑ የስብሰባ እና የተለያዩ መርሃግብር ዝግጅቶች መቀነሳቸውን በመናገር ገቢያቸው በእጅጉ መቀነሱን አስታውቀዋል።
በሰሜን ቨርጂኒያ የንግድ ም/ቤት ሊቀመንበር የሆኑት ማርክ ከሪየር ለምክርቤቱ አዲስ መፍትሄ ማምጣት አለብን ሲሉ አሳስበዋል።