የአርሊንግተን ካውንቲ ፖሊስ ዛሬ ዲሴምበር 17 ባወጣው መግለጫ ለመጪው አዲስ አመት ስምንት አዳዲስ የፍጥነት መቆጣጠሪያ የትራፊክ ካሜራዎችን እስከ ጃንዋሪ 6 2025 በህዝብ ትምህርት ቤቶች አቅራቢያ መትከል መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ይህም በትምህርት ተቋማት አካባቢ ተሽከርካሪዎች በሚኖራቸው አላግባብ ፍጥነት የሚያስከትለውን ጉዳት መቀነስ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
እነዚህ አዳዲስ ካሜራዎች የሚተከሉባቸው አካባቢዎችም የሚከተሉት ናቸው፡፡
- ወደሰሜን ሲጓዙ በ 700 block of N. George Mason Drive
- ወደሰሜን ሲጓዙ በ 1600 block of N. Glebe Road
- ወደ ምዕራብ ሲጓዙ በ 4100 block of Lorcom Lane
- ወደ ደቡብ ሲጓዙ በ 2500 block of S. Arlington Ridge Road
- ወደ ምስራቅ ሲጓዙ በ 5800 block of Williamsburg Boulevard
- ወደ ደቡብ ሲጓዙ በ 1000 block of N. McKinley Road
- ወደ ምስራቅ ሲጓዙ በ3500 block of 2nd Street S.
- ወደሰሜን ሲጓዙ በ 1600 block of N. Veitch Street ናቸው፡፡
ከዚህ ቀደም በሰራነው ዘገባ ላይ በ2024 መስከረም ወር ላይ 10 አዳዲስ የፍጥነት መቆጣጠሪያ ካሜራዎች ተገጥመው ወደ ስራ እንደገቡ ይታወቃል፡፡
በመጪው ወር ስራ የሚጀምሩት ስምንቱ አዳዲስ ካሜራዎች ከጃንዋሪ 6 እስከ ፌብሯሪ 4 2025 ለአሽከርካሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲሆን በሚል የማስጠንቀቂያ ትኬት የሚልኩ ሲሆን ከፎእብሯሪ 5 ጀምሮ ግን የ100$ የቅጣት ወረቀት እንደሚልኩ በመግለጫው ተገልጿል፡፡