
የሞንጎምሪ ካውንቲ ፖሊስ ዛሬ ሰኞ ጁን 16 ማምሻውን ባወታው መግለጫ የ21 አመት ወጣት የሆነውን ቅዱስ ሙሉጌታን አፋልጉኝ ብሏል። የፖሊስ መግለጫ እንደሚያሳየው ቅዱስ ቁመቱ 5 ጫማ ከ8 ኢንች ሲሆን ክብደቱ 180 ፓውንድ ነው ተብሏል። ቅዱስ ቡናማ የአይንና ጥቁር የጸጉር ቀለም አለው።
ቅዱስ ለመጨረሻ ጊዜ የታየው ትላንት ጁን 15 2025 ምሽት 8pm ላይ በ8800 ማንቸስተር ሮድ ሲልቨር ስፕሪንግ አቅራቢያ ነው። በወቅቱም ጥቁር ኖርዝፌስ ሁዲ ሹራብ በመሮጫ ቁምጣ አርጎ ነበር ተብሏል።
ምናልባትም የሜሪላንድ ታርጋዋ 7GB1393 የሆነ ባለ 4 በር ቀይ ቶዮታ ካምሪ ሴዳን መኪና ይዞ ሊሆን እንደሚችል በመግለጫው ተነግሯል። የቅዱስን መገኛ የሚያውቅ ሰውም ለፖሊስ በስልክ ቁጥር 301-279-8000 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል።
