
በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የሚከበረውንና የባርነት አገዛዝን በይፋ ያስቀረው የጁንቲንዝ በዓል ተከትሎ በርካቶች በአሁኑ ወቅት በስደተኞች ላይ እየደረሰ ካለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በማወዳደር ያነጻጽሩታል፡፡
በጁን 19 1865 ፤ የባርነት አገዛዝ እንዲቀር በይፋ በህግ ከጸደቀ ከ2 አመት በሗላ በግልቭስተን ቴክሳስ የነበሩ ባሮች ግን ይህ አዋጅ ሳይነገራቸው ለ2 አመት ያህል ነጻነታቸው ተነፍጓቸው ሲኖሩ ነበር፡፡ ከሁልት አመት በኋላ የአንድነት ኃይሎች ጋልቭስቶን ቴክሳስ በመሄድ ይህን ህግ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረጋቸውን ተከትሎም ቀኑ በጥቁሮች ዘንድ እንደልዩ በዓል እንዲታሰብ ሆኗል፡፡ የፌደራል መንግስትም በቀድሞው ፕሬዘደንት ባይደን ወቅት አገር አቀፍ በዓል እንዲሆን ተደርጓል፡፡

ይህ ቀንም ለብዙዎች ህጋዊ ነጻነት ወይንም ህጋዊነት በራሱ የሚተገብረው አካል ከሌለ በፍጹም በቂ እንዳልሆነ ማሳያ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በበርካታ ስደተኞች ላይ ህጋዊ ወረቀት ወይንም ህጋዊ የትምህርት ቪዛ እያላቸው በድንገት ህጋዊነታቸውን የሚያጡበት መንገድ ማህበረሰብ የተስማማበትንና የህጋዊና ህገወጥ መለያ መስመርን ከማደብዘዝ አልፎ የሰብዓዊ መብት ቀውስ ይፈጥራል፡፡
ከዚህም አልፎ ተርፎ እንዲህ ያሉ ጨቋኝ ህጎች ተረቀው በመንግስት ተግባራዊ ሲደረጉ ማየት የህጋዊነትን ትርጉም ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል፡፡ በዚህም አለ በዛ ግን የሰው ልጆች ሁሌም ከጨቋኞቻቸው ቀንበር ለመውጣት ሲታገሉ ይኖራሉ በዚህ ትግላቸውም በርካታ ደጋፊዎች ይኖሯቸዋል፡፡ በዲሲና አካባቢውም በርካታ የስደተኛ መብት ተቆርቋሪዎችና ደጋፊዎች ይህን ቀን ከጥቁር አሜሪካውያን በተጨማሪ በዚህ ዘመን የተገፉትን በማሰብና በማገዝ እንደሚያሳልፉ አሳውቀዋል፡፡