@ethiopique202 (21)

የዲሲ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ብርያን ሽዋልብ ከሰሞኑ ባወጡት መግለጫ የሶስተኛ ወገን የሓይል አቅራቢዎች ነን የሚሉ ሰዎች ከፔፕኮም ሆነ ከሌላ ድርጅት ዕውቅና ውጪ በር ለበር በመዞር በርካታ ነዋሪዎችን ያለፈቃዳቸው እጅግ ውድ የሆነ ፕሮግራም ውስጥ እያስገቧቸው እንደሆነና ነዋሪዎች ለአላስፈላጊ ወጪ እየተዳረጉ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡  

በርካታ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩትም እነዚህ ሰዎች ፍጹም ህገወጥ በሆነ መንገድ ሰዎችን እንደሚመዘግቡና አልፎ አልፎም የሰዎቹን መስማማት ሳያገኙ ያለሰዎቹ እውቅና ወደራሳቸው ድርጅት እንደሚያስገቧቸው ታውቋል፡፡  

የዲሲ ነዋሪዎች እንዲህ ያሉ ሰዎች በቤትዎ ከመጡና በተለይም በቢልዎ ላይ ቅናሽ እንደሚያገኙ ከነገሩዎ በፍጹም እንዳያምኗቸውና ይልቅስ ራሳቸው ደንበኞች አስፈላጊውን ምርምር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡ እነዚህ ወንጀለኞች በአካል ከመምጣት ባለፈ በስልክ በመደወል ወይንም በፖስታ ቤት በደብዳቤ የሚያሳምን ወይንም የሚያስጨንቁ ደብዳቤዎችን በመላክ ሰዎችን ወደራሳቸው ተቋም እንዲሄዱ ያደርጋሉ፡፡ በተለይ የቋንቋ ችግር ያለባቸውን ስደተኞች አባብለው ካስማሙ በሗላ የኤሌክትሪክ ክፍያቸውን በሶስትና አራት እጥፍ እንዲከፍሉ ያስገድዷቸዋል፡፡

የዚህ ወንጀል ሰለባ የሆኑ ሰዎች ደሞ በቀጥታ እነዚህ ድርጅቶችጋ ወይንም ለፔፕኮና ዋሽንግተን ጋዝ በመደወል ደንበኝነትዎን ማቋረጥ ይችላሉ፡፡ ተጨማሪ እገዛ ካስፈለገዎት ደሞ ይህን ሊንክ በመጫን ወይንም በስልክ ቁጥር (202) 727-3071 በመደወል አልያም በኢሜይል consumer.protection@dc.gov, ከዲሲ የህዝብ አገልግሎት ክፍል ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡ 

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.