@ethiopique202 (23)

የዋሽንግተን ኢንግሊሽ ሴንተር ላለፉት አስርት አመታት በዲሲና አካባቢው ላሉ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ስደተኞች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ እንደተለመደውም በዚህ የበጋ ወራት ለአዋቂዎች የ6 ሳምንት ትምህርት አዘጋጅቷል፡፡ በዚህ ፕሮግራም የቋንቋ ችሎታቸው ከጀማሪ እስከ መካከለኛና አድቫንስድ ያሉትን ይቀበላል፡፡ አይ መክፈል አልችልም አቅሙ የለኝም ለሚሉ ደግሞ ተቋሙ የስኮላርሺፕ ዕድል አዘጋጅቷል፡፡ 

የኢትዮጲክ ባልደረባ ያነጋገሯቸው የተቋሙ የፕሮግራም ዳይሬክተር ጄሲ ኤብሬሶል እንዳስረዱት ተቋሙ ተማሪዎችን ለመቀበል የስደተኝነት ወረቀት ወይንም ሌሎች ተያያዥ ዶክመንቶችን የማይጠቅ ሲሆን ለስኮላርሽፕ የሚያመለክቱትንም ራሳቸው በተናገሩት ላይ ተመስርቶ በዕምነት ስኮላርሺፑን እንደሚሰጥና እንደ ፔይስታብና የገቢ ማስረጃ እንደማይጠይቅ ነግረውናል፡፡ 


ማስታወቂያ

የበጋ ትምህርት በጁላይ 14 የሚጀምር ሲሆን ትምህርቱ ባሉት ውስን ቦታዎች ቀድመው የተመዘገቡትን ይዞ እንደሚቀጥልም ታውቋል፡፡ በዚህ መልካም ዕድል ለመጠቀምም ተማሪዎች ይህን ሊንክ በመጫን ወደ ተቋሙ ድረ ገጽ መሄድና መመዝገብ ይችላሉ፡፡  www.washingtonenglish.org/students

ተቋሙ በተጨማሪ ማንኛውም ሰው ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጧት 9፡30 እስከ ምሽት 7፡00am ባለው ጊዜ በዳውንታውን ዲሲ በሚገኘው ቢሯቸው በመሄድ ተቋሙን መጎብኘት እንደሚችል ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል፡፡  

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.