01/10/2025
IMG_20191208_185552

አርብ ዲሴምበር 20/2024

የኢትዮጲክ ባልደረቦች በተለያዩ አመታት ከቤተሰቦቻቸውጋ ያሳለፏቸውንና ከተለያዩ ምንጮች ያገኟቸውን እነዚህን መረጃዎች በማንበብ ልጆችዎ ለክረምት ያላቸውን እረፍት አብራችሁ በመዝናናት ማሳለፍ ትችላላችሁ።

የናሽናል ዙ- ዙ ላይት

የናሽናል ዙ ላይት ከኖቨምበር 22 ጀምሮ እስከ ጃንዋሪ 4 የሚዘልቅ በመካነ-አራዊቱ በሙሉ ያሸበረቁ መብራቶችና የሌዘር ብርሀን ትሪዒት የሚደረግበት ፕሮግራም ሲሆን በሳምንት ቀናትና ቅዳሜ ከ5pm እስከ 9pm እንዲሁም እሁድ ከ5pm እስከ 8pm ይከናወናል።

ከዛሬ ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሰኞ ዲሴምበር 23 ከዛ በኋላ ደሞ ለገና አርፈው ከዲሴምበር 26 እስከ ዲሴምበር 30 ፕሮግራም ያላቸው ሲሆን ከላይ በተጠቀሱት ሰዓታት አገልግሎታቸውን ይሰጣሉ። ከአዲሱ አመት በኋላ ደሞ ለ2 ቀናት ጃንዋሪ 3 እና ጃንዋሪ 4 ብቻ ክፍት የሚሆኑ ይሆናል። የመግቢያ ዋጋው 6$። መኪና ይዘው ለመሄድ ካሰቡ የፓርኪንግ 30$ ከማስከፈሉም በላይ ኦንላይን አስቀድመው መግዛት ይኖርብዎታል።

ቦታኒክ ጋርደን የበዓል ትርዒት

የዩ ኤስ ቦታኒክ ጋርደን ዘንድሮም እንደተለመደው ታሪካዊ ቦታዎችንና ሌሎች ቅርሶችን የሚያሳይበትና እጽዋቶቹን የሚያሳይበት ዝግጅቱን ከኖቨምበር 28 ጀምሮ እስከ ጃንዋሪ 5፣ 2025 ድረስ ያከናውናል። በዚህ ትር ዒትላይም ከእጽዋቱና ከቅርጻ ቅርጾቹ በተጨማሪም ሞዴል ባቡሮች ለዕይታ እንደሚቀርቡ ተናግረዋል።፡ ይህ ትር ዒት ታዲያ ከኖቨምበር 28 ጀምሮ እስከ ጃንዋሪ 5 2025 ድረስ ከጠዋቱ 10am እስከ 5pm ክፍት ይሆናል። በዚህ ትርዒት ለመገኘት ምንም ክፍያም ሆነ የቅድሚያ ምዝገባ አያስፈልግም።

ብሄራዊ የገና ዛፍ (National Christmas Tree)

ይህ የገና ዛፍና በዙሪያው ያሉ በርካታ የመብራት ትር ዒቶች ከዲሴምበር 5 እስከ ጃንዋሪ 1 ክፍት ናቸው። ከዋናው ትልቁ ዛፍ ዙሪያ በአሜሪካ 50 ግዛቶችና ሌሎች ወሰኖች ስም የተዘጋጁ አነስተኛ ዛፎች ለዚህ ትር ዒት መድመቅ ትልቅ ድርሻ አላቸው።
ይህ ትር ዒት ሁሌም ጸሀይ ከጠለቀችበት ሰዓት አንስቶ እስከ ምሽት 10pm ድረስ ክፍት ይሆናል። መግቢያው በነጻ ነው።


የዲሲ የበዓል ገበያ (DC holiday market)

አመታዊው የዳውንታውን ዲሲ ሆሊዴይ ማርኬት ዘንድሮም ለ20ኛ ጊዜ ተከፍቷል:: ይህ ገበያ በኖርዝ ዌስት ዲሲ F Street ላይ በ 7th ና 9th Streets, ይከናወናል:: ይህ ገበያ የዲሲ ሰፈሮች በተለይም ፔን ኳርተርና ቻይናታውን ድምቀት ይሰጣል:: ገበያው ከኖቨምበር 22 እስከ ዲሴምበር 23 ክፍት ይሆናል:: ለቴንክስጊቪንግ ብቻ ዝግ ይሆናል::

መግቢያው በነጻ

የጌይሎርድ ናሽናል ሆቴል የገና ዝግጅቶች

በናሽናል ሀርበር የሚገኘው የጌይሎርድ ሆቴል ዘንድሮም ለበአሉ በርካታ የመብራት ትዕይንቶችንና ፕሮግራሞችን አዘጋጅቷል። ከነዚህም ታዋቂውዎቹ ከ3 ሚልየን በላይ አምፖሎች ያሉት የመብራት ትር ዒትና የሬንዲር ስካቬንጀር ኸንት ይገኙበታል። መግቢያቸው በነጻ ነው።

ዋትኪንስ ሪጅናል ፓርክ- የመብራት ፌስቲቫል

ከመኪናዎ ሳይወርዱ በፓርኩ ውስጥ የሚጓዙበትና የተዘጋጀውን የመብራት ፌስቫል የሚኮመኩሙበት ፕሮግራም ነው። ለመግባት ኦንላይን 10$ ቦታው ላይ 15$ ትኬት ይሸጣል።

ዋሽንግተን ዲሲ ቴምፕል የመብራት ፌስቲቫል (ሞርሞን ቸርች)


የናሽናል ዲሲ ቴምፕል በየአመቱ የሚያዘጋጀው በ500 ሺህ አምፖሎች የሚያጌጠው የብርሀን ፌስቲቫል ዘንድሮም ከዲሴምበር 5 እስከ ጃንዋሪ 1 ይከናወናል።፡የዘንድሮውን ለየት የሚያደርገው ለመታደም ትኬት አያስፈልገዋም። ማንኛውም ሰው በመኪና ወይንም በእግር ከምሽት 4:45pm ጀምሮ እስከ 9:0)pm በቦታው በመሄድ መታደም ይቻላል። 9900 Stoneybrook Dr, Kensington, MD 20895

ኦልድ ታውን አሌክሳንድርያ

ኦልድ ታውን አሌክሳንድርያ እንኳን በበዓል በአዘቦት ቀንም የሚያምር የአውሮፓ ትንሽ ከተማ የሚመስል ድባብ ያለበት አካባቢ ነው። በበአል ሰሞን ደሞ የበለጠ ይደምቅና ለፎቶ የሚያምር ባክግራውንድ ይሆናል።፡

የገና ዛፋቸው ከኖቨምበር 23 ጀምሮ ተተክሏል። በ400 ሺህ አምፖሎችም ተንቆጥቁጧል። መግቢያው በነጻ ነው።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *