ወንጀልን ለመከላከል ይረዳ ዘንድ የሞንጎምሪ ካውንቲ ካውንስል ለነዋሪዎችና ለንግድ ማዕከላት የሴኩሪቲ ካሜራ እንዲያስገጥሙ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ቢል አዘጋጅተው አቅርበዋል።
ይህ ቢል ከፀደቀ ማንኛውም የካውንቲው ነዋሪ ለሚያስገጥመው የሴኩሪቲ ካሜራ ካውንቲው ወጪውን ይጋራል። ይህን ፕሮግራም በዋናነት የሚይዘው የሞንጎምሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት ፕሮግራሙ በዋናነት የት ሰፈሮች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይወስናል። ይህን ቢል ያቀረቡት የካውንስል አባላት ክሬይግ ራይስ፤ ሲድኒ ካትዝና ካውንስል ፕሬዘደንት ጌብ አልቦርኖዝ ሲሆኑ ካውንስል አባል ዊል ጃዋንዶ፤ ናንሲ ናቫሮና ቶም ኸከርም በአጋዥነት ተሳትፈዋል።
ይህ ፕሮግራም በዋናነት የሴኩሪቲ ካሜራ ለማስገጠም አቅም ለሌላቸው ነዋሪዎችና የንግድ ድርጅቶች መፍትሄ ይሆናል ተብሏል። ይህ አይነት አሰራር እንደ ዋሽንግተን ዲሲ ባሉ ሌሎች ቀጠናዎች የተለመደ አሰራር ነው ተብሏል።
ይህን ቢል ለማጽደቅ የሚረዳ የህዝብ ግብዓት ለመሰብሰብ ለጁላይ 12፤ 2022 ቀጠሮ ተይዟል።