የ2026 የአለም ዋንጫ በዲሲ ዛሬ ይወሰናል

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶስት አገራት አዘጋጅነት የሚካሄደው የ2026 የፊፋ የአለም ዋንጫ በአሜሪካ ሜክሲኮና ካናዳ ውስጥ 48 ተፋላሚ አገራትን ይዞ ይከናወናል። ዋሽንግተን ዲሲና ቦልቲሞር በጋራ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ ከሚፎካከሩ ከተሞች አንዱ ናቸው።
ይህንን የአለም ዋንጫ ለማስተናገድ ደሞ ፊፋ በሶስቱ አገራት ውስጥ ያሉ 16 ከተሞችን ይመርጣል። ከዚህም ውስጥ 10 በአሜሪካ ካናዳና ሜክሲኮ እያንዳንዳቸው 3 ከተሞችን ይዘው ይሳተፋሉ። በሶስቱ አገራት መካከል የአለም ዋንጫን ለማስተናገድ ያመለከቱ ከተሞች የሚከተሉት ናቸው። አትላንታ፤ ቦስተን፤ ሲንሲናቲ፤ ዳላስ፤ ዴንቨር፤ ሂውስተን፤ ካንሳስ ሲቲ፤
ሎስ አንጀለስ፤ ማያሚ፤ ናሽቪል፤ ኒውዮርክ/ኒውጀርሲ፤ ኦርላንዶ፤ ፊላደልፊያ፤ ሳንፍራንሲስኮ፤ ሲያትል፤ ቦልቲሞር/ዋሽንግተንዲሲ፤ ጓዳላሃራ፤ ሜክሲኮ ሲቲ፤ ሞንቴሪ፤ኤድሞንተን፤ ቶሮንቶና ቫንኩቨር ናቸው።
የአስተናጋጅ ከተሞች ምርችጫ ዛሬ ከ5pm ጀምሮ ይከናወናል።

ፕሮግራሙን በቀጥታ ለማየት ይህን ሊንክ ይጫኑ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.