12/12/2024
FXehSbNXoAAa2Gl

የቦልቲሞር-ዋሽንግተን አካባቢ የናሽናል ዌዘር ሰርቪስ ዛሬ ከሰዓት ከባድ ዝናብ ንፋስና በረዶ ከቀላቀለ ውሽንፍርጋ እንደሚኖር በትዊተር ገፁ ጠቁሟል።

ይህን ተከትሎ የየከተማው ፖሊስና አደጋ ተከላካዮች ለነዋሪዎቻቸው የጥንቃቄ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

ከነዚህ አንዱ የታኮማ ፓርክ ፖሊስ በዚህ ሳቢያ ለሚደርሱ ጉዳቶችና አደጋዎች እንደ ግዝፈታቸው የሚደወሉባቸውን ስልኮች አጋርተዋል።

የ911 ስልኮች እንዳይጨናነቁም ለወደቁ ዛፎች ለተዘጉ መንገዶች ነዋሪዎች በ301-270-1100 እንዲደውሉ ጠይቀዋል።ለመብራት መቋረጥ ፔፕኮን በ877-737-2662 ማግኘት ይችላሉ።

አለርት ዲሲ የተባለው የዲሲ መንግስት አውቶማቲክ የትዊተር አካውንት ደሞ ነዋሪዎች ስላክቸውንና ሌሎች ኤሌክትሮኒክ እቃዎቻቸውን ቻርጅ አርገው እንዲዘጋጁ ጠይቀዋል። በተጨማሪም በጎርፍ ከመንዳት እንዲታቀቡና ውሽንፍሩ እስኪያልፍ መጠለያ ፈልገው እንዲያሳልፉ ጠይቀዋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት