ዛሬ ምሽቱን በጣለው ዝናብና መብረቅ በርካታ ጉዳቶች በዲሲና አካባቢው መድረሱ ታውቋል። የዲሲ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ተከላካይ ድርጅት ወደ 6pm ላይ በትዊተር ገፁ እንዳሳወቀው 2 ተሳፋሪዎች ያሉበት መኪና ላይ ዛፍ እንደወደቀባቸውና ከመኪናቸው በመስሪያቤቱ ሰራተኞች እርዳታ እንደወጡ አሳውቋል።
በተጨማሪም በ1300 block Morse St NE. ዛፍ መኪና ላይ እንደወደቀ ነገር ግን የተጎዳ ሰው እንደሌለ አሳውቋል።
በተጫማሪም በዮርክታውንና ሰድበሪ ኖርዝዌስት ዛፍ ወድቆ መንገዱን እግቶ የነበረ ሲሆን በርካታ የኤሌክትሪክ መስመሮችም ተበጥሰው መሬት ወድቀዋል።
በተጨማሪም 3200 block Cathedral Ave NW አካባቢ ተበጥሶ በወደቀ የኤሌክትሪክ ገመድ ምክንያት ሁለት መኪኖች በእሳት ሙሉለሙሉ ታቃጥለዋል።
ከዲሲ በተጨማሪ ቤተስዳ አካባቢ የወደቀ የኤሌክትሪክ መስመር ሲቀጣጠል የሚያሳይ ቪዲዮ በነዋሪውች ተለቋል።
በተጨማሪም በርካታ መንገዶች በወደቁ ዛፎች ተሞልቷል። የትራፊክ መብራቶች አገልግሎት መስጠት አቁመዋል። የየካውንቲው ፖሊሶች አሽከርካሪዎች በጥንቃቄ እንዲሾፍሩ አስገንዝበዋል።
ስቶርሙ በኮሌጅ ፓርክ ደሞ አንድን ቤት ሁለት ቦታ ከፍሎታል።
በኦልኒ ሜሪላንድ ስቶርሙ ከባድ ጉዳት በቤትና ንብረት ላይ አድርሷል።
በርካታ ዛፎችም ተገንድሰዋል።
ከ20-30 ቤቶችም ፈርሰዋል። በርካታ ቤተሰቦች ያለመጠለያ ቀርተዋል::